የጦሓራ ትርጉም

0
376
  1. ቋንቋዊ ትርጉሙ፡-

ጦሓራ የዓረብኛ ቃል ትርጉሙ ከማንኛውም ቆሻሻ መፅዳት ማለት ነው፡፡

ትምህርታዊ ትርጉሙ፡- “ሀደሥን”ና ቆሻሻን ማስወገድ ነው:: “ሀደሥን” ማስወገድ ሲባል ሰላትን የሚከለክልን ባህሪ ከአካል ማውረድ ማለት ሲሆን ትልቁ ከሆነ ሙሉ አካልን ትንሹ ከሆነ ደግሞ የዉዱእ አካሎችን በውሃ በመታጠብ ውሃ ከጠፋ ወይም መጠቀም ካልተቻለ ሸሪዓው ባዘዘው መልኩ አፈርን በመጠቀም ነው፡፡

ቆሻሻን ማስወገድ ሲባል ደግሞ ነጃሳን ከአካል ከልብስና ከቦታ ማስወገድ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አካላዊ ጦሓራ ሁለት አይነት ነው ማለት ነው፡፡

=> “ሀደስን” ማስወገድ አካልን ብቻ የሚመለከት ሲሆን

=>ቆሻሻን ማስወገድ ደግሞ አካልን ልብስንና ቦታን የሚያካትት ነው፡፡

“ሀደስ” ሁለት አይነት ነው፡፡

1 ትንሹ “ሀደስ” ውዱእን የሚያስገድድና

2 ትልቁ “ሀደስ” ደግሞ ገላ ትጥበትን የሚያስከትል ነው፡፡

ነጃሳ ደግሞ ሶስት አይነት ነው፡፡

1 መታጠቡ ግድ የሚሆን፣

2 ውሃ መርጨት በቂ የሚሆንና

3 ማበስ ብቻ የሚበቃው ናቸው፡፡

2 የጦሓራ ወሳኝነቱና ክፍሎቹ

የጦሓራ ወሳኝነትና ክፍሎቹ፡-

ጦሓራ የሰላት መክፍቻና ከመስፈርቶቹ አሳሳቢው ነው፡፡ የአንድ ስራ መስፈርት ደግሞ የግድ ከስራው መቅደም አለበት፡፡

ጦሓራ በሁለት ይከፈላል፦

አንደኛው ክፍል፡- ውስጣዊ ፅዳት ሲሆን ልብን ከሽርክ ከኃጢአትና ከማንኛውም ውስጣዊ ጉድፍ ማፅዳት ማለት ነው፡፡ የልብ ፅዳት ከአካል ፅዳት የበለጠ አሳሳቢ ጉዳይ ነው:: እንዲያውም የልብ ቆሻሻ እያለ አካል ሊፀዳ አይችልም፡፡

አላህ እንዲህ ብሏል ፡-

‹‹አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፡፡››(ተውባህ 28)

ሁለተኛው ክፍል አካላዊ ፅዳት፡-

ይህ ክፍል ተከታታይ በሆኑ ነጥቦች የሚብራራ ነው፡፡