አምስቱን የእስምልና ማዕዘናትን ማብራራት ከእነዚህም ውስጥ የመጀመሪያውና ዋነኛው «ሸሀዳ» ወይም ምስክርነት ሲሆን፤ እርሱም ከአላህ በስተቀር በእውነት ሊያመልኩት የሚገባ አምላክ አለመኖሩን፤ ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር ነው። የሁለቱን የምስክርነት ቃላት ትርጉም ማብራራት እና የላኢላሀ ኢለላህ መስፈርቶችን ከማሰረጃ ጋር መግለፅ ያስፈልጋል። ማንኛውም ሰዉ ወደ ኢስላም መግባት ከፈለገ እነዚህን ሁለት የምስክርነት ቃላት መስጠት ይጠበቅበታል፡፡እንደሚታወቀዉ ምስክርነት በእዉቀት ላይ የተመሰረተ መሆኑ የግድ ነዉና ጥቅል በሆነ መልኩም የእነዚህን የምስክርነት ቃላት መልዕክት ሊያዉቅ ይገባል፡፡
(አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢለላህ) የሚለው የቃለ ተውሂድ ምስክርነት ትርጓሜ ‹ከአላህ በስተቀር በሀቅ አምልኮ የሚገባው እንደሌለ እመሰክራለሁ ማለት ሲሆን፡፡
(ወአሽሀዱ አነ ሙሀመደን ረሱሉላህ) የሚለው ምስክርነት ደግሞ ሙሀመድ ه የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸዉን እመሰክራለሁ ማለት ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
(እነሆ! ከአላህ ሌላ አምልኮ የሚገባው አለመኖሩን እወቅ፤ ስለ ስህተትህም ለምዕመናንም ምህረትን ለምን..) ሙሐመድ19
“ላ ኢላሀ” የሚለው የአረፍተ ነገሩ ክፍል ከአላህ ውጪ የሚመለኩ አማልክትን በሙሉ ውድቅ የሚያደርግ «ማፍረስ ወይም ነፍይ» ሲሆን
“ኢለላህ” የሚለው የአረፍተ ነገሩ ክፍል ደግሞ አምልኮ ለአንድ አላህ ብቻ መሆኑንና ምንም አጋር እንደሌለው የሚያረጋግጥ «ማጽደቅ ወይም ኢስባት» ነው።
‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› የሚለው የምስክርነት ቃል መልዕክት ከአላህ በቀር አምልኮ የሚገባው የለም ብሎ ማመን ነው፡፡ ይህ ምስክርነት ሁለት መሰረታዊ ክፍሎች አሉት፡- ‹ላ ኢላሀ› ወይም ‹አምላክ የለም› የሚለዉ ክፍል አምልኮ የሚገባዉ ማንም እንደሌለ የሚያመለክት ሲሆን ጣኦትን መካድ (ኩፍር ቢጧጉት) ተብሎ ይጠራል፡፡ ‹ኢለላህ› ‹ከአላህ በስተቀር› የሚለዉ ደግሞ አምልኮን (ኢባዳን) ለአላህ ብቻ ማዋል እንደሚገባ የሚያሳይ ክፍል ነዉ፡፡ ይህ ክፍል ደግሞ በአላህ ማመን (አል ኢማን ቢላህ) ይባላል፡፡ አላህ አንዲህ ይላል፡-