ቀደር አራት ደረጃዎች እንዳሉት በመረጃዎችና በዑለማዎት ንግግር የፀደቀ ነው፡፡
አንደኛው ደረጃ፡- የአላህ እውቀት
አላህ ያለን የሌለን ሊሆን የሚችልንና ሊሆን የማይችልን ነገሮች ያለፈን የወደፊትን ያልሆነ ነገር ቢሆን ምን እንደሚሆን እንደሚያውቅ ማመን፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል
{ لِتَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ وَأَنَّ اللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيْءٍ عِلْمًا } (الطلاق : 12)
ቡኻሪና ሙስሊም ከኢብን ዓባስ በአስተላለፉት ሀዲስ ነቢዩ ሰዐወ ስለአጋሪዎች ህፃን ልጆች እጣ ፈንታ ተጠይቀው እንዲህ ሲሉ መልሰዋል “አላህ ምን ሊሰሩ እንደሚችሉ ያውቃል፡፡”[1]
ሁለተኛው ደረጃ፡- አላህ እስከ እለተ ትንስአ የሚፈፀሙትን ነገሮች እንደለ መፃፍ፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል
{ أَلَمْ تَعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا فِي السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ إِنَّ ذَلِكَ فِي كِتَابٍ إِنَّ ذَلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ } ( الحج : 70)
{ وَكُلَّ شَيْءٍ أحْصَيْنَاهُ فِي إِمَامٍ مُبِينٍ } ( يس : 12)
ከላይ ባሳለፍነው ሀዲስ አላህ ሰማያትና ምድርን ከመፍጠሩ ሃምሳ ሺ አመት በፊት ውሳዎቹን እንደፃፈ ተገልጿል፡፡
ሶስተኛው ደረጃ፡- ሁሉም ነገር በርሱ ፍላጐት ስር መሆኑንና እሱ የፈለገው የሚከሰት ያልፈለገው ደገሞ ሊከሰት የማይችል መሆኑን ማመን፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል
{ إِنَّمَا أَمْرُهُ إِذَا أَرَادَ شَيْئًا أَنْ يَقُولَ لَهُ كُنْ فَيَكُونُ } (يس : 82)
{ وَمَا تَشَاءُونَ إِلَّا أَنْ يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ } (التكوير : 29)
ቡኻሪና ሙስሊም ከአቡ ሑረይራ በአስተላለፉት ሀዲስ ነቢዩ ሰዐወ እንዲህ ብለዋል “ማናችሁም “ጌታዬ ከፈለግክ ማረኝ ፍላጐትህ ከሆነ እዘንልኝ” እንዳትሉ በቁርጠኝነት ለምኑት አላህ የፈለገውን የሚፈፀምና አስገዳጅ የሌለው ነው፡፡”[2]
አራተኛው ደረጃ፡- አላህ እያንዳንዱን ነገር ፈጣሪ መሆኑንና ማንኛውም ስራና ሰሪውን ተንቀሳቃሽና እንቅስቃሴውን አስገኝ መሆኑን ማመን፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል
{ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ وَكِيلٌ } (الزمر : 62)
{ وَاللَّهُ خَلَقَكُمْ وَمَا تَعْمَلُونَ } (الصافات : 96)
ቡኻሪ ከኢምራን ኢብን ሁሰይን በአስተላለፉት ሀዲስ ነቢዩ ሰዐወ እንዲህ ብለዋል
« كان الله ولم يكن شيء غيره وكان عرشه على الماء وكتب في الذكر كل شيء وخلق السماوات والأرض »
“አላህ ነበር ከርሱ ሌላ ምንም ሳይኖር፣ ዐርሹም ውሃ ላይ ነበር፣ በመዝገቡ ሁሉን ነገር ፅፎ ሰማያትና ምድርን ፈጠረ፡፡”[3]
በቀደር ላይ ያለን እምነት ለማረጋገጥ በነዚህ አራት የቀደር ደረጃዎች ማመን ግዴታ ነው፡፡ በነዚህ ደረጃዎች ያለመነ ቀደር ላይ የሚኖረው እምነት የተስተካከለ ሊሆን አይችልም፡፡
[1] ቡኻሪ 1384 ሙስሊም 2659
[2] ቡኻሪ 7ዐ39 ሙስሊም 2679
[3] ቡኻሪ 3ዐ2ዐ