?የሚጥም ትዳር
በሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን አንደበት [አላህ ይዘንላቸው]
? ? ?
«አንድ ባል ሚስቱን በጥሩ አያያዝ ተኗኗራት የሚባለው ከሷ ጋር በአንድ ፍራሽ ላይ አንድ ለሃፍ [ኮምፎርት፣ ብርድ ልብስና የመሳሰሉትን የመኝታ ልብስ በጋራ ] ለብሶ መተኛቱ ነው።
ምክንያቱም የመልእክተኛው [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ፈለግ ይኸ ነበርና።
ነገር ግን እነዚያ ባሎቹም ለብቻቸው፣ ሚስቶችም ለየብቻቸው የሚተኙ ሰዎች፤ አንዳንዴም ከዚህ በከፋ ሁኔታ እሱ በተለየ ክፍል እሷም በተለየ ክፍል የሚተኙ (የሚያድሩ) ከሆነ ያለምንም ጥርጥር ይህ ከትዳር ጓደኛ ጋር በመጥፎ ሁኔታ መኗኗር ” سوء المعاشرة” ይባላል።»
[ይኸ ደግሞ አላህ ያዘዘንን በመልካም ሁኔታ የመኗኗር ኑዛዜን ይጥሳል።]
አላህም እንዲህ ብሏልኮ☞
”هُنَّ لِبَاسٌ لَّكُمْ وَأَنتُمْ لِبَاسٌ لَّهُنَّ“
«እነርሱ ለናንተ ልብሶች ናቸው፤ እናንተም ለነርሱ ልብሶች ናችሁ፡፡» አልበቀራህ☞187 : البقرة
———————
ምንጭ☞⇘
من اقوال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله:
في التعليق على صحيح مسلم
/ ج2 / ص182
============
?የዐለማችን ውብ ሴት
☞ ቁርኣንን በአእምሮዋ በመሸምደድ የሃፈዘችውና በውስጡ ያዘለውንም ህግጋት በተግባር ያዋለች…
☞ የአላህ መልእክተኛን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በመጎዳኘት በኢስላም ታሪክ ወደር የማይገኝለትን ታሪክ ያስመዘገቡ ሴቶችን (ሰሃቢያትን) አርኣያዎቿ ያደረገች …
☞ ከዚህም ከዚያም አየጠሯት የጥብቅነቷን፣ የንፅህናዋንና የአይን-አፋርነቷን ሂጃብ ሊያስጥሏት ለሚጣሯት ጎትጓቾች ጥሪ መስሚያ የሌላት፣ ቦታ የማትሰጣቸው…
☞ ለወላጆቿ መልካሚት በመሆን እንደ ልጅም እን እናትም የምትንከባከባቸውና ለክብራቸው፣ ለስነልቦናቸው ቅድሚያ የምትሰጥ…
☞ ክብሩና ልዕልናው የላቀው አላህን በማያስቆጣ ነገር ላይ ባሏን የምትታዘዝ፤ ጥሩ ረዳትና ጓደኛም በመሆን የታማኝነት ፍቅርን የምትለግሰው…
☞ ሀያሉ አላህ ፊት በመቆም ልትሰግድለትና መልካም ምንዳውን እንዲሁም ትሩፋቱን ልትለምነው ስትል እንቅልፏን በመቀነስ ጣፋጭ ከሆነው ጣዕሙ ራሷን የምታቅብ…
☞ የአላህን ተባረከ ወተዓላ ውዴታና በረከቱን በመሻት የፍላጎት ፆሞችን የምትፆም…
☞ ምላሷን የምትጠብቅና የሰዎችን ክብር በሚነካ ጉዳይ ላይ የማትዘፈቅ…
☞ ክብሩና ልዕልናው የላቀው አላህ ሀራም ወዳደረገው ነገር ባለመመልከት ራሷን የምታርቅ…
☞ ኢስላምን ለመርዳት ስትል፣ አላህን ግዴታ ያደረገባትን ትእዛዝ ለመፈፀም ስትል በአላህ መንገድ ላይ ባሏን፣ ልጇን፣ ገንዘቧንና ህይወቷንም መስዋእት የምታደርግ…
አላህ ሆይ ሙስሊም እንስቶቻችንን ባርክልን። ሁሉን ባያሟሉ እንኳን የቻሉትን ያህል የፈፀሙትን ስራዎቻቸውን ተቀበላቸው። አጋር የሚሆን ወንድም፣ ደጋፊ የሚሆን ባልና፣ ተባባሪ የሚሆን ማህበረሰብ ወፍቃቸው። በመንገድህም ላይ አፅናቸው።
آمين