ተውራት፣ ኢንጂልና ሌሎች መፃህፍት በሰዎች የተዛቡ ሲሆን
ቁርአን ግን የተጠበቀ ነው፡፡
የመፅሐፍ ባለቤቶች የአላህ ቃል ስለማዛባታቸው
አላህ የመፅሐፍ ባለቤቶች ንግግሩን እንዳዛቡና እንደቀየሩ ተናግሯል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል
{ أَفَتَطْمَعُونَ أَنْ يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِنْ بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ وَهُمْ يَعْلَمُونَ } (البقرة : 75)
‹‹(አይሁዶች) ከነሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሚለውጡት ሲኾኑ ለናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?›› አል በቀራህ 75
{ مِنَ الَّذِينَ هَادُوا يُحَرِّفُونَ الْكَلِمَ عَنْ مَوَاضِعِهِ } (النساء : 46)
‹‹ከነዚያ አይሁዳውያን ከኾኑት ሰዎች ንግግሮችን ከስፍራዎቹ የሚያጣምሙ አልሉ፡፡›› ኒሳእ 46
ስለክርስቲያኖችም ሲናገር አላህ እንዲህ ብሏል
{ وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَى أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِمَّا ذُكِّرُوا بِهِ فَأَغْرَيْنَا بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَسَوْفَ يُنَبِّئُهُمُ اللَّهُ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ }{ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِمَّا كُنْتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَنْ كَثِيرٍ } ( المائدة : 14 ، 15)
‹‹ከእነዚያም እኛ ክርስቲያኖች ነን ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት፡፡ ስለዚህ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብንና ጥላቻን ጣልንባቸው፡፡ አላህም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ በእርግጥ ይነግራቸዋል፡፡ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን (ሙሐመድ) በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ ›› ማኢዳህ 14-15
ስለመጨመር ማስረጃ
{ فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ يَكْتُبُونَ الْكِتَابَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَذَا مِنْ عِنْدِ اللَّهِ لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا فَوَيْلٌ لَهُمْ مِمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌ لَهُمْ مِمَّا يَكْسِبُونَ } (البقرة : 79)
‹‹ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት (ኃጢኣት) ወዮላቸው፡፡›› አል በቀራህ 79
ስለመቀነስ ማስረጃው
{ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِمَّا كُنْتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ } (المائدة : 15)
‹‹የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን (ሙሐመድ) በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ ›› ማኢዳህ 15
{ قُلْ مَنْ أَنْزَلَ الْكِتَابَ الَّذِي جَاءَ بِهِ مُوسَى نُورًا وَهُدًى لِلنَّاسِ تَجْعَلُونَهُ قَرَاطِيسَ تُبْدُونَهَا وَتُخْفُونَ كَثِيرًا } (الأنعام : 91)
‹‹(እንዲህ) በላቸው፡- «ያንን ብርሃንና ለሰዎች መሪ ኾኖ ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትኾኑ ማን አወረደው᐀ (የወደዳችኋትን) ትገልጿታላችሁ ብዙውንም ትደብቃላችሁ፡፡›› አል አንዓም 91
የተውራትና የኢንጂል መበረዝና ማስረጃዎቻቸው
ከላይ የተጠቀሰው በጥቅሉ የመፅሐፍ ባለቤቶች የአላህን ንግግር እንደበረዙ ሲሆኑ በተለይ ደግሞ ተውራትና ኢንጂል እንደተዛቡ የሚጠቁሙ መረጃዎችም አሉ፡፡
{ قُلْ مَنْ أَنْزَلَ الْكِتَابَ الَّذِي جَاءَ بِهِ مُوسَى نُورًا وَهُدًى لِلنَّاسِ تَجْعَلُونَهُ قَرَاطِيسَ تُبْدُونَهَا وَتُخْفُونَ كَثِيرًا وَعُلِّمْتُمْ مَا لَمْ تَعْلَمُوا أَنْتُمْ وَلَا آبَاؤُكُمْ قُلِ اللَّهُ ثُمَّ ذَرْهُمْ فِي خَوْضِهِمْ يَلْعَبُونَ } (الأنعام : 91)
‹‹(እንዲህ) በላቸው፡- «ያንን ብርሃንና ለሰዎች መሪ ኾኖ ሙሳ ያመጣውን መጽሐፍ ክፍልፍሎች የምታደርጉት ስትኾኑ ማን አወረደው᐀ (የወደዳችኋትን) ትገልጿታላችሁ ብዙውንም ትደብቃላችሁ፡፡ እናንተም አባቶቻችሁም ያላወቃችሁትን ተስተማራችሁ›› አል አንዓም 91
ዑለማዎች ይህን አንቀፅ ሲተረጉሙ እንዲህ ብለዋል “ሙሳ ያመጣውን መፅሐፍ የፈለጋችሁትን ለማዛባትና እንዲሁም ስለነቢዩ ሰዐወ የተነገረውንም ባህሪ ለመቀየር ያመቻችሁ ዘንድ በተበታተነ ወረቀት ታደርጋላችሁ፡፡”
አላህ እንዲህ ብሏል
{ أَفَتَطْمَعُونَ أَنْ يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِنْ بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ } (البقرة : 75)
‹‹(አይሁዶች) ከነሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሚለውጡት ሲኾኑ ለናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?›› አል በቀራህ 75
በዚህ አንቀጽ ትርጉም ዙሪያ ሱድይ እንዲህ ብለዋል “ያዛቡት መፅሐፍ ተውራትን ነው፡፡” ኢብን ዘይዳም እንዲህ ብለዋል “አላህ እነሱ ላይ የወረደውን ተውራት ሀላልን ሀራም ሀራሙን ሀላል ሀቅን ሐሰት ሐሰቱን ሀቅ በማድረግ ያዛባሉ፡፡”
ኢንጂል እንደተበረዘ ማስረጃው
وَمِنَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّا نَصَارَى أَخَذْنَا مِيثَاقَهُمْ فَنَسُوا حَظًّا مِمَّا ذُكِّرُوا بِهِ فَأَغْرَيْنَا بَيْنَهُمُ الْعَدَاوَةَ وَالْبَغْضَاءَ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَسَوْفَ يُنَبِّئُهُمُ اللَّهُ بِمَا كَانُوا يَصْنَعُونَ }{ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِمَّا كُنْتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَنْ كَثِيرٍ } (المائدة : 14-15)
‹‹ከእነዚያም እኛ ክርስቲያኖች ነን ካሉት የጠበቀ ቃል ኪዳናቸውን ያዝን፡፡ በእርሱም ከታዘዙበት ነገር ፈንታን ተውት፡፡ ስለዚህ እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስ በመካከላቸው ጠብንና ጥላቻን ጣልንባቸው፡፡ አላህም ይሠሩት የነበሩትን ሁሉ በእርግጥ ይነግራቸዋል፡፡ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን (ሙሐመድ) በእርግጥ መጣላችሁ፡፡›› አል ማኢዳህ 14-15
የተፍሲር ምሁራሮች የሁለተኛውን አንቀፅ ትርጉም እንዲህ ያብራራሉ “የቀየሩት ያዛቡትንና አላህ ላይ የቀጠፉትን ያብራራል፡፡ ሆኖም መግለፁ ጥቅም የሌለውን ሌሎች ብዙ ማዛባቶችን ደግሞ ዝም ብሎ ያልፋል፡፡”[1]
እነዚህ አንቀፆች ተውራትና ኢንጂል የተበረዙ መሆናቸውን ይገልፃሉ፡፡ የሙስሊም ዑለማዎችም ተውራትና ኢንጂል የተዛቡ በመሆናቸው ይስማማሉ፡፡
ቁርአን ከመበረዝ የተጠበቀ በአላህ ጥበቃ ስር ያለ ስለመሆኑና ማስረጃዎቹ
ቁርአን በአላህ ጥበቃ ጥር በመሆኑ ከዚህ በፊት በነበሩ መፃህፍት ላይ የደረሰው ብረዛና ክለሳ ሊገጥመው አልቻለም፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል
{ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ } (الحجر : 9)
‹‹እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡›› ሂጅር 9
ጠበሪይ በዚህ አንቀፅ ትርጉም ዙሪያ እንዲህ ብሏል “ቁርአን ውስጥ የሌለ እንዳይጨመር ከሱም እንዳይቀነስ እኛ ጠባቂዎቹ ነን፡፡”[2]
በሌሎችም አንቀፆች ቁርአንን ያኀናው ያብራራውወና ከሐሰቶሀት የጠበቀው መሆኑን ይናገራል፡፡
{ لَا يَأْتِيهِ الْبَاطِلُ مِنْ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِ تَنْزِيلٌ مِنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍ } ( فصلت : 42)
‹‹ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ው፡፡›› ፉሲለት 42
{ الر كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِنْ لَدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ } ( هود : 1)
‹‹አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርኣን) አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ (የተወረደ) ነው፡፡›› ሁድ 1
{ لَا تُحَرِّكْ بِهِ لِسَانَكَ لِتَعْجَلَ بِهِ }{ إِنَّ عَلَيْنَا جَمْعَهُ وَقُرْآنَهُ } (القيامة : 16 ، 17)
‹‹በእርሱ (በቁርኣን ንባብ) ልትቸኩል ምላስህን በእርሱ አታላውስ፡፡ (በልብህ ውስጥ) መሰብሰቡና ማንበቡ በእኛ ላይ ነውና፡፡›› ቂያማህ 16-17
እነዚህ አንቀፆች አላህ ቁርአን ከወረደ ጀምሮ ወደርሱ እስኪመለስ ድስ ቃሉንም ሆነ ትርጉሙን በሚገባ እንደጠበቀው ይጠቁማሉ፡፡ ይህን ቁርአን ከመጀመሪያው አላህ ነቢዩን ሰዐወ ካስተማረ በኃላ በልባቸው እንዲይዙ አደረገ፡፡ ከዚያም በአስተምህሮዋቸው እንዲብራራ ካደረገ በኃላ ትውልድ በተተካካ ቁጥር ታማኝ ሰዎች በሽምደዳና በፅሑፍ እንዲጠብቁት በማድረግ ከሐሰት ተጠብቆ ህፃናትም ሽማግሌም ልክ ነቢዩ ላይ እንደወረደው እንዲያነቡት አደረገ፡፡
ዑለማዎች ተውራት መበረዝ የተቻለበትንና ቁርአንን መበረዝ ግን ያልተቻለበትን ሚስጥር ተናግረዋል፡፡ አቡ ዓምር አዳኒይ ከአቢል ሀሰን አልሙንታብ እንዳስተላለፉት “አንድ ቀን ከቃዲ አቢ ኢስሃቅ ኢስማኤል ኢብን ኢስሃቅ አብሬ ሳለሁ እንዲህ ተጠየቁ “እንዴት በተውራት ሰዎች ማዛባት ተቻለ እንዴትስ በቁርአን ህዝቦች ማዛባት አልተቻለም?” ቃዲም እንዲህ ሲሉ መለሱ “አላህ ስለተውራት ሰዎች እንዲህ አለ
{ بِمَا اسْتُحْفِظُوا مِنْ كِتَابِ اللَّهِ } (المائدة : 44)
‹‹ … ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ…›› ማኢዳህ 44
ጥበቃን በነሱ ኃላፊነት አዳረገ ስለዚህም መበረዝ ተቻለ ስለቁርአን ህዝቦች ግን አላህ እንዲህ አለ
{ إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ } (الحجر : 9)
‹‹እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡›› ሂጅር 9
ስለዚህም ማዛባት አልተቻለም፡፡”
[1] ኢብኑ ከሲር 3/63
[2] ተፍሲር ኢብን ጀሪር 7/14