አንደኛ፡- ቀደር ትርጉሙና ማስረጃዎቹ
ቀደር በአላህ የቀድሞ እውቀት የተመሰረተ ፍጥረታት ከመገኘታቸው በፊት የሚወስንላዠው ውሳኔ ነው፡፡ በቀደር ማመን ከኢማን ማዕዘናት አንዱ ስለመሆኑ የቁርአንና የሀዲስ ማስረጃዎች አብራርተዋል፡፡
ከቁርአን መረጃዎች
አላህ እንዲህ ብሏል
{ إِنَّا كُلَّ شَيْءٍ خَلَقْنَاهُ بِقَدَرٍ } (القمر : 49)
{ وَكَانَ أَمْرُ اللَّهِ قَدَرًا مَقْدُورًا } (الأحزاب : 38)
{ وَخَلَقَ كُلَّ شَيْءٍ فَقَدَّرَهُ تَقْدِيرًا } (الفرقان : 2)
ከሀዲስ ብዙ መረጃዎ ውስጥ በተደጋጋሚ የተገለፀው ጅብሪል ሀዲስ አንዱ ነው፡፡ ሙስሊም ከአብደላህ ኢብን ዓምር ኢብን ዓስ እንዳስተላለፉት ነብዩ ሰዐወ እንዲህ ብለዋል
« كتب الله مقادير الخلائق قبل أن يخلق السماوات والأرض بخمسين ألف سنة وقال : وكان عرشه على الماء »
“አላህ ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠር በሃምሳ ሺህ አመት በፊት የተወሰነላቸውን ፅፏል፡፡”[1]
በቀደር ማመን ሰሃቦችና ከነሱም በኃላ የመጡ ህዝቦች የለምንም ሃሳብ ልዩነት የተስማሙበት ጉዳይ ነው፡፡ ኢማም ሙስሊም እንዳስተላለፉት ጣውስ እንዲህ ብለዋል “ሰሃቦች እያንዳንዱ ክስተት በቀደር ነው በሚለው እምነት ላይ ነበሩ፡፡” አብደላህ ኢብን ዑመርም ነቢዩ ሰዐወ እንዲህ ብለዋል ሲል ሰምቼሃለሁ “ማንኛውም ነገር ጉብዝናና ስንፍና ሳይቀር በአላህ ውሳኔ ነው፡፡”[2]
ኢማም አነወዊይ እንዲህ ብለዋል “ቁርጥ ያሉ የቁርአንና ሀዲስ መረጃዎች የሰሃቦች የቀደምትና የዘመኑ ዑለማዎች ሁሉ ስምምነት ቀደርን ያፀድቃሉ፡፡”
[1] ሙስሊም 2653
[2] ሙስሊም 2655