በመፅሐፍት የማመን ሸሪዓዊ ድንጋጌና ማስረጃዎቹ

1
97

አላህ ባወዳቸው መፃህፍት በአጠቃላይ ማመን ከኢማን ማዕዘናት አንዱ በመሆኑ ኢማን ሊረጋገጥ የሚችለው በመፅሐፍቶች ሲታመን ነው፡፡ ለዚህ ማስረጃ የሚጠቀሱት ቁርአንና ሀዲስ ናቸው፡፡ ከቁርአን አላህ እንዲህ ይላል

{ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا آمِنُوا بِاللَّهِ وَرَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي نَزَّلَ عَلَى رَسُولِهِ وَالْكِتَابِ الَّذِي أَنْزَلَ مِنْ قَبْلُ وَمَنْ يَكْفُرْ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا بَعِيدًا } (النساء : 136)

‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልክተኛው በዚያም በመልክተኛው ላይ ባወረደው መጽሐፍ በዚያም ከበፊቱ ባወረደው መጽሐፍ እመኑ፡፡ በአላህና በመላእክቱም፣ በመጽሐፎቹም፣ በመልክተኞቹም፣ በመጨረሻውም ቀን፣ የካደ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡›› አል ኒሳእ 136

በዚህ አንቀፅ ላይ አላህ እግሮቹን በርሱና በመልዕክተኛው መሐመድ፣ መልዕክተኛው ላይ በወረደው ቁርአን እንዲሁም ከሱ በፊት በነበሩት መልዕክተኞች ላይ በወረዱ መፅሐፍት ለምሳሌ በተውራት ኢንጂልና ዘቡር እንዲያምኑ ካዘዘ በኃላ በመጨረሻም ከነዚህ የእምነት ማዕዘናት በአንዱ እንኳን ያስተባበለ የጐላ ጥመትን እንደትጠመመና ከትክክለኛው መንገድ እንዳፈነገጠ ገለፀ፡፡ በሌላም አንቀፅ እንዲህ ይላል

{ لَيْسَ الْبِرَّ أَنْ تُوَلُّوا وُجُوهَكُمْ قِبَلَ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ وَلَكِنَّ الْبِرَّ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَالْمَلَائِكَةِ وَالْكِتَابِ وَالنَّبِيِّينَ } (البقرة : 177)

‹‹መልካም ሥራ ፊቶቻችሁን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞር አይደለም፡፡ ግን መልካም ሥራ በአላህና በመጨረሻው ቀን፣ በመላእክትም፣ በመጻሕፍትም፣ በነቢያትም፣ ያመነ…›› አል በቀራህ 177

በሁሉም መፃህፍት ማመንን ለማፅናት ሲልም አማኞች የመፅሐፍት ባለቤቶችን በዚሁ መልኩ እንዲያናግሩ አዘዘ፡፡

{ قُولُوا آمَنَّا بِاللَّهِ وَمَا أُنْزِلَ إِلَيْنَا وَمَا أُنْزِلَ إِلَى إِبْرَاهِيمَ وَإِسْمَاعِيلَ وَإِسْحَاقَ وَيَعْقُوبَ وَالْأَسْبَاطِ وَمَا أُوتِيَ مُوسَى وَعِيسَى وَمَا أُوتِيَ النَّبِيُّونَ مِنْ رَبِّهِمْ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍ مِنْهُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ } (البقرة : 136)

«በአላህና ወደኛ በተወረደው (ቁርኣን) ወደ ኢብራሂምም ወደ ኢስማዒልና ወደ ኢስሐቅም ወደ ያዕቁብና ወደ ነገዶቹም በተወረደው በዚያም ሙሳና ዒሳ በተሰጡት በዚያም ነቢያት ሁሉ ከጌታቸው በተሰጡት ከነርሱ በአንድም መካከል የማንለይ ስንኾን አመንን፤ እኛም ለርሱ (ለአላህ) ታዛዦች ነን» በሉ፡፡ (አል በቀራህ 136)

ከሀዲስ

በመፃህፍት ማመን ግዴታ ለመሆኑና ከኢማን ማዕዘናት ውስጥ አንድ ለመሆኑ ክፍል አንድ ላይ የተጠቀሰው የጂብሪል ሀዲስ መረጃ ይሆናል፡፡