በመላዕክት ማመን

0
128

አንደኛ ነጥብ

መልአክ ምን ማለት እንደሆነ የፍጥረታቸው መሰረት ባህሪዎቻቸውና መለያዎቻቸው

መልአክ ምን ማለት እንደሆነ

መላኢካ የተሰኘው የዓረብኛ ቃል መለክ ለሚሰኘው ቃል ብዜት ሲሆን ኡሉካ ከሚለው ቃል የተወሰደ ነው ትርጉሙም መልዕክት ማለት ነው፡፡

መልአኮች ከአላህ ፍጥረቶች ውስጥ ሲሆኑ ብርሃናዊ ስውር አካል ያላቸው፣ በመልካም ምስሎች መመሰል የሚችሉ፣ ከባድ ኃይልና ፈጣን እንቅስቃሴ ያላቸው ቁጥራቸውን ከአላህ ሌላ ማንም የማያውቀው እጅግ በጣም ብዙ ናቸው፡፡

አላህ እርሱን ለማምለክና ትዕዛዛቱን ለመፈፀም ምቹ አድርጎ የመረጣቸው በመሆናቸው ያዘዛቸውን ከመፈፀም ውጭ ቅንጣት ታህል ትዕዛዛቱን አይጥሱም፡፡

የፍጥረታቸው መሰረት፡-

አላህ መልአኮች የፈጠረው ከብርሃን ነው፡፡ አዒሻ ረዐ በአስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ ሰዐወ እንዲህ ብለዋል አላህ መልአኮችን ከብርሃን፣ አጋንኖችን ከእሳት ነበልባልና አደምን ከተገለፀላቸው ነገር ፈጠረ፡፡”[1]

ባህሪዎቻቸው፡-

ቁርአንና ሀዲስ ውስጥ ብዙ የመላእኮች ባህሪያት ተዘርዝረዋል ከነዚህም ውስጥ፡-

  • ሀይልና ጥንካሬ፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል

{ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنْفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ } (التحريم : 6)

‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ፡፡›› ተህሪም 6

ጅብሪልንም ሲገልፅ እንዲህ ይላል

{عَلَّمَهُ شَدِيدُ الْقُوَى } (النجم : 5)

‹‹ኀይሎቹ ብርቱው (መልአክ) አስተማረው፡፡›› አል ነጅም 5

 { ذِي قُوَّةٍ عِنْدَ ذِي الْعَرْشِ مَكِينٍ } (التكوير : 20)

‹‹የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡›› ተክዊር 2ዐ

  • ግዙፍ አካል

عائشة رضي الله عنها وقد سألت النبي صلى الله عليه وسلم عن معنى قوله تعالى { وَلَقَدْ رَآهُ بِالْأُفُقِ الْمُبِينِ } (التكوير : 23) فقال : « إنما هو جبريل لم أره على صورته التي خلق عليها غير هاتين المرتين رأيته منهبطا من السماء سادا عظم خلقه ما بين السماء إلى الأرض » صحيح مسلم برقم (177)

አዒሻ ረዐ ነብዩን ሰዐወ ስለሚከተለው { وَلَقَدْ رَآهُ بِالْأُفُقِ الْمُبِينِ } (التكوير : 23) አንቀፅ ማብራሪያ ጠይቀው እንዲህ ሲሉ መልሰውላቸዋል “ይህ ማለት ጅብሪል ነው፡፡ በነዚህ ሁለት ጊዜዎች እንጂ በተፈጠረበት ቅርፁ አይቼው አላውቅም ከሰማይ ወርዶ አካሉ በሰማይና በምድር መካከል ሞልቶ ተመለከትኩት፡፡”[2]

ኢማም አህመድ እንደዘገቡት አብደላህ ኢብን መስዑድ እንዲህ ብለዋል “የአላህ መልልዕክተኛ ጂብሪልን በተፈጠረበት ቅርፁ ስድስት መቶ ክራፎች ኖሮት ተመለከቱት እያንዳንዱ ክንፎች አድማስን የሸፈኑ ሲሆን ከክንፎቹ አላህ የሚያውቃቸው … ይርገፈገፋሉ”

ጃቢር ኢብን አብደላህ በአስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ ሰዐወ እንዲህ አሉ

« أذن لي أن أحدث عن ملك من ملائكة الله من حملة العرش إن ما بين شحمة أذنه وعاتقه مسيرة سبعمائة عام »  سنن أبي داود : (5 / 96) ، برقم (4727)

“አርሽን ተሸካሚዎች ከሆኑ መላዕክት ስለ አንዱ መልአክ እንድናገር ተፈቅዶልኛል ከጆሮው እስከትከሻው ያለው ርቀት የሰባት መቶ አመት ጉዞ ነው፡፡”[3]

     በፍጥረትና በመጠን አንዱ ከሌላው የሚለይ ሲሆን ሁለት ክንፎች፣ ሶስት ክንፎች፣ አራት ክንፎችና ስድስት መቶ ክንፎች ያላቸውም አሉ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል

{ الْحَمْدُ لِلَّهِ فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ جَاعِلِ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا أُولِي أَجْنِحَةٍ مَثْنَى وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ يَزِيدُ فِي الْخَلْقِ مَا يَشَاءُ } (فاطر : 1)

‹‹ምስጋና ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፣ መላእክትን ባለ ሁለት ሁለት፣ ባለ ሶስት ሶስትም፣ ባለ አራት አራትም ክንፎች የኾኑ መልክተኞች አድራጊ ለኾነው አላህ ይገባው፡፡ በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል፡፡›› ፋጢር 1

  • በጣም የተዋቡና ያጣሩ ናቸው፡፡ አላህ ስለ ጅብሪል ሲናገር እንዲህ ብሏል

{عَلَّمَهُ شَدِيدُ الْقُوَى }{ ذُو مِرَّةٍ فَاسْتَوَى } (النجم : 5 ، 6)

‹‹ኀይሎቹ ብርቱው (መልአክ) አስተማረው፡፡ የዕውቀት ባለቤት የኾነው (አስተማረው፤ በተፈጥሮ ቅርጹ ኾኖ በአየር ላይ) ተደላደለም፡፡›› አል ነጅም 5-6

ኢብኑ አባስ እንዲህ አሉ “ዙሚረቲ” ባለ መልካም ውበት ማለት ነው፡፡” ቀታዳህም እንዲህ ብለዋል “ረዥምና ውብ ማለት ነው”፡፡

አላህ ሴቶች ዩሱፍን አይተው እሱን በማድነቅ የተናገሩትን ሲናገር እንዲህ ይላል

{ فَلَمَّا رَأَيْنَهُ أَكْبَرْنَهُ وَقَطَّعْنَ أَيْدِيَهُنَّ وَقُلْنَ حَاشَ لِلَّهِ مَا هَذَا بَشَرًا إِنْ هَذَا إِلَّا مَلَكٌ كَرِيمٌ } (يوسف : 31)

‹‹ባዩትም ጊዜ አደነቁት፡፡ እጆቻቸውንም ቆረጡ፡፡ አላህም ጥራት ይገባው፡፡ ይህ ሰው አይደለም፡፡ ይህ ያማረ መልአክ እንጅ ሌላ አይደለም አሉ፡፡›› ዩሱፍ 31

እነዚህ ሴቶች ይህን ያሉት መልአኮች ውብ መሆናቸው የታወቀ በመሆኑ ነው፡፡

  • አላህ መልአኮችን የተከበሩና ታዛዦች ሲልም ገልጿቸዋል

{ بِأَيْدِي سَفَرَةٍ }{ كِرَامٍ بَرَرَةٍ } (عبس : 15 ، 16)

‹‹በጸሐፊዎቹ (መላእክት) እጆች (ንጹሕ የተደረገች)፡፡ የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት (ጸሐፊዎች እጆች)፡፡››  ዓበሰ 15-16

{ وَإِنَّ عَلَيْكُمْ لَحَافِظِينَ }{ كِرَامًا كَاتِبِينَ } (الانفطار : 10 ، 11)

‹‹በእናንተ ላይ ተጠባባቂዎች ያሉባችሁ፤ ስትኾኑ፤ የተከበሩ ጸሐፊዎች የኾኑ፤ (ተጠባባቂዎች)፡፡›› አል ኢንፊጣር 1ዐ-11 

  • አይን አፋሮች ናቸው

ነብዩ ሰዐወ ሰለዑስማን ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል “መልአኮች የሚያፍሩትን ሰው አላፍረውምን?”

  • እውቀትም መልአኮች ከተገለፁበት ባህሪያት አንዱ ነው፡፡ አላህ መልአኮችን ሲያናግር እንዲህ ብሏል

{ قَالَ إِنِّي أَعْلَمُ  ما لا تعلمون } (البقرة : 30)

(አላህ) «እኔ የማታውቁትን ነገር አውቃለሁ» አላቸው፡፡ አል በቀራህ 3ዐ

እሱ የሚያውቀውን እንደማያውቀው ቢገልፅም እነሱም አዋቂዎች መሆናቸውን አፅድቋል፡፡ አላህ ስለጂብሪል እንዲህ ይላል

{عَلَّمَهُ شَدِيدُ الْقُوَى (النجم : 5 )

‹‹ኀይሎቹ ብርቱው (መልአክ) አስተማረው፡፡›› አል ነጅም 5

ጠበሪይ እንዲህ ብለዋል ጂብሪል ይህን ቁርአን ለመሐመድ አስተማረ ስለዚህ ጂብሪል በእውቀትና በአስተማሪነት ተገልጿል ማለት ነው፡፡

እነዚህና የመሳሰሉ ከፍተኛ ደረጃ እንዳላቸው የሚጠቀሙ የቁርአንና የሀዲስ መረጃዎች አሉ፡፡

መለያዎቻቸው፡-

መላእኮች ከሰዎችና ጋኔኖች የሚለዩባቸው የተለያዩ መለያዎች አሏቸው ከነዚህም ውስጥ፡-

  • ማረፊያቸው ሰማይ ላይ ሲሆን ወደ ምድር የሚወርዱት የአላህን ትእዛዛት ለመፈፀምና እንዲያከናውኑ የተሰጣቸውን ጉዳዮች ለማከናወን ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል

{ يُنَزِّلُ الْمَلَائِكَةَ بِالرُّوحِ مِنْ أَمْرِهِ عَلَى مَنْ يَشَاءُ مِنْ عِبَادِهِ } (النحل : 2)

‹‹ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል፡፡›› አል ነህል 2

{ وَتَرَى الْمَلَائِكَةَ حَافِّينَ مِنْ حَوْلِ الْعَرْشِ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ } (الزمر : 75)

‹‹መላእክትንም በጌታቸው ምስጋና ቀላቅለው የሚያጠሩ ሲኾኑ በዐርሹ ዙሪያ ከባቢዎች ኾነው ታያለህ፡፡» አል ዙመር 75

አቡ ሁረይራ በአስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል

« يتعاقبون فيكم ملائكة بالليل ، وملائكة بالنهار ، ويجتمعون في صلاة الصبح وصلاة العصر ، ثم يعرج الذين باتوا فيكم فيسألهم الله وهو أعلم بهم كيف تركتم عبادي ؟ فيقولون : تركناهم وهم يصلون ، وأتيناهم وهم يصلون »  صحيح البخاري برقم (555) وصحيح مسلم برقم (632)

“በቀንና ሌሊት መላኢኮች ይተካኩባቹሃል በሱብሂ ሰላት ወቅትም ይሰባሰቡና ሌሉቱን ከእናንተ ጋር ያደሩት ወደ ሰማይ ያርጋሉ አላህም እያወቀ ባሮቼን በምን ሁኔታ ትታቿቸው መጣችሁ በማለት ሲጠይቃቸው ስንመጣም ስንሄድም እየሰገዱ ነበር” በማለት ይመልሱለታል፡፡

በዚህ ርዕስ የመጡ ጥቅሶች በጣም ብዙ ናቸው

  • በእንስትነት አይገለፁም፡፡ አላህ መላኢኮችን በእንስት ለገለፁ ከሃዲያን እየወቀሰ እንዲህ ይላል

{ وَجَعَلُوا الْمَلَائِكَةَ الَّذِينَ هُمْ عِبَادُ الرَّحْمَنِ إِنَاثًا أَشَهِدُوا خَلْقَهُمْ سَتُكْتَبُ شَهَادَتُهُمْ وَيُسْأَلُونَ } (الزخرف : 19)

‹‹መላእክትንም እነርሱ የአልረሕማን ባሮች የኾኑትን ሴቶች አደረጉ፡፡ ሲፈጠሩ ነበሩን? መመስከራቸው በእርግጥ ትጻፋለች፡፡ ይጠየቃሉም፡፡›› ዙኽሩፍ 19

{ إِنَّ الَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ لَيُسَمُّونَ الْمَلَائِكَةَ تَسْمِيَةَ الْأُنْثَى } (النجم : 27)

‹‹እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት መላእክትን በሴት አጠራር ይጠራሉ፡፡›› አል ነጅም 27

  • አላህን በፍፁም የማያምፁ ኃጢአት የማይፈፅሙና አላህ ታዛዥ አድርጎ የፈጠራቸው ናቸው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-

{ لَا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ } (التحريم : 6)

‹‹አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡›› ተህሪም 6

 { لَا يَسْبِقُونَهُ بِالْقَوْلِ وَهُمْ بِأَمْرِهِ يَعْمَلُونَ } (الأنبياء : 27)

‹‹በንግግር አይቀድሙትም፤ (ያላለውን አይሉም)፡፡ እነርሱም በትእዛዙ ይሠራሉ፡፡›› አል አንቢያህ 27

  • በአምልኮ ላይ ማይደክሙና ማይሰለቹ ናቸው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል

{ وَمَنْ عِنْدَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ }{ يُسَبِّحُونَ اللَّيْلَ وَالنَّهَارَ لَا يَفْتُرُونَ } (الأنبياء : 19 ، 20)

‹‹እርሱ ዘንድ ያሉትም (መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፡፡ አይሰለቹምም፡፡ በሌሊትና በቀንም ያጠሩታል፤ አያርፉም፡፡›› አል አንቢያህ 19-2ዐ

{ فَإِنِ اسْتَكْبَرُوا فَالَّذِينَ عِنْدَ رَبِّكَ يُسَبِّحُونَ لَهُ بِاللَّيْلِ وَالنَّهَارِ وَهُمْ لَا يَسْأَمُونَ } (فصلت : 38)

‹‹ቢኮሩም እነዚያ በጌታህ ዘንድ ያሉት (መላእክት) በቀንም በሌሊትም ለእርሱ ያወድሳሉ፡፡ እነርሱም አይሰለቹም፡፡›› ፉሲለት 38

ከላይ የተጠቀሱት ከፊል ከሰዎችና ከጋኔኖች የሚለዩባቸው መለያዎች ናቸዉ፡፡ በጥቅሉ መልአክት የተለዩ ፍጡርሮች በመሆናቸው ሰዎችና ጋኔናች አንዱ ከሌላው መለያ ባህሪዎች እንዳላቸው ሁሉ እነሱም ከሰዎችና ጋኔኖች የሚለዩባቸው ባህሪዎች አሏቸው፡፡

[1] ሙስሊም ዘግበውታል 2996

[2] ቡኻሪ 3ዐ61 ሙስሊም 174 ቲርሚዚ 3283 አህመድ 1/395

[3] አቡ ዳውድ 4727