በመላኢኮች የማመን ወሳኝነት፣ የእምነቱ ሁኔታና ማስረጃዎቹ

0
165

መላእኮች የማመን ወሳኝነት

መላእኮች ማመን ከእምነት ማዕዘናት አንዱ በመሆኑ ለኢማን ወሳኝ ነው፡፡ አላህ በቁርአኑ እንዲሁም ነብዩ ሰዐወ በሀዲሳቸው አብራርተውታል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል

{ آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنْزِلَ إِلَيْهِ مِنْ رَبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ كُلٌّ آمَنَ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ } (البقرة : 285)

‹‹መልክተኛው ከጌታው ወደ ርሱ በተወረደው አመነ፡፡ ምእምኖቹም (እንደዚሁ)፡፡ ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ በመልክተኞቹም፡፡›› አል በቀራህ 285

በመላእኮች ማመንንና በተቀሩ የኢማን ማዕዘናት ማመን አላህ በመልዕክተኛው ላይ ያወረደውና ግዴታ ያደረገው መሆኑንና እነሱም ይህን ትዕዛዝ መፈፀማቸውን ተናገረ፡፡

በሌላም አንቀፅ አላህ እንዲህ ይላል፡-

{ لَيْسَ الْبِرَّ أَنْ تُوَلُّوا وُجُوهَكُمْ قِبَلَ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ وَلَكِنَّ الْبِرَّ مَنْ آمَنَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَالْمَلَائِكَةِ وَالْكِتَابِ وَالنَّبِيِّينَ } (البقرة : 177)

‹‹መልካም ሥራ ፊቶቻችሁን ወደ ምሥራቅና ምዕራብ አቅጣጫ ማዞር አይደለም፡፡ ግን መልካም ሥራ በአላህና በመጨረሻው ቀን፣ በመላእክትም፣ በመጻሕፍትም፣ በነቢያትም፣ ያመነ ነው፡፡›› አል በቀራህ 177

ይህ አንቀፅ ውስጥ በተዘረዘሩት ነገሮች ማመን የመልካም ነገር መገላጫ መሆኑን ገለፀ፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች የመልካም ተግባር ቁንጮ እንዲሁም የኢማን ቅርንጫፎች የሚበቅሉበት ግንድ ነው፡፡ በአንፃሩ ደግሞ በነዚህ መሰረቶች የካደ በአላህ የካደ መሆኑን እንዲህ በማለት ይገልፃል፡፡

{ وَمَنْ يَكْفُرْ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ وَرُسُلِهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا بَعِيدًا } (النساء : 136)

‹‹በአላህና በመላእክቱም፣ በመጽሐፎቹም፣ በመልክተኞቹም፣ በመጨረሻውም ቀን፣ የካደ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡›› አል ኒሳእ 137

እነዚህን መሰረቶችን ያስተባበለን በክህደት መረረጁና መጥመትመት መዘፈቃቸውን መግለፁ በመላዕኮች ማመን ዋና የእምነት ማዕዘን መሆኑንና ይህን አለማመን ደግሞ ከኢስላም የሚያስመጣ መሆኑን ያሳያል፡፡

የነብዩም ሰዐወ ሀዲስ ይህን የሚያጠናክር ሲሆን የጅብሪል ሀዲስ በመባል በሚታወቀው ሙስሊም ከኡመር ኢብኑል ኸጣብ በአስተላለፈው ሀዲስ እንዲህ ይላል

« بينما نحن عند رسول الله صلى الله عليه وسلم ذات يوم إذ طلع علينا رجل شديد بياض الثياب ، شديد سواد الشعر ، لا يرى عليه أثر السفر ، ولا يعرفه منا أحد ، حتى جلس إلى النبي صلى الله عليه وسلم ، فأسند ركبتيه إلى ركبتيه ، ووضع كفيه على فخذيه ، وقال : يا محمد ! أخبرني عن الإسلام ؟ فقال رسول الله صلى الله عليه وسلم : الإسلام أن تشهد أن لا إله إلا الله وأن محمدًا رسول الله صلى الله عليه وسلم ، وتقيم الصلاة ، وتؤتي الزكاة وتصوم رمضان ، وتحج البيت إن استطعت إليه سبيلا . قال : صدقت . قال : فعجبنا له ، يسأله ويصدقه . قال : فأخبرني عن الإيمان ؟ قال : أن تؤمن بالله ، وملائكته ، وكتبه ، ورسله ، واليوم الآخر . وتؤمن بالقدر خيره وشره . قال : صدقت . قال : فأخبرني عن الإحسان . قال : أن تعبد الله كأنك تراه ، فإن لم تكن تراه فإنه يراك . قال : فأخبرني عن الساعة ؟ قال ما المسؤول عنها بأعلم من السائل . قال : فأخبرني عن أماراتها ؟ قال : أن تلد الأمة ربَّتها . وأن ترىالْحُفاة العُراة ، العَالة ، رِعاءَ الشاء ، يتطاولون في البنيان . قال : ثم انطلق فلبثت مليًّا ثم قال لي : يا عمر ! أتدري من السائل ؟ قلتَ : الله ورسوله أعلم . قال : فإنه جبريل ، أتاكم يعلمكم دينكم »  صحيح مسلم برقم (8)

“ከዕለታት አንድ ቀን ከአላህ መልዕክተኛ ሰዐወ ጋር ተቀምጠን ሳለ አንድ ፀጉሩ በጣም የጠቆረና በጣም ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው ብቅ አለና ነብዩ ሰዐወ ዘንድ ጉልበቱን ከጉልበታቸው በማስተካከል እጆቹን ታፋዎቹ ላይ በማሳረፍ ተቀመጠና እንዲህ አላቸው “ሙሐመድ ሆይ ስለ ኢስላም ንገሩኝ? የአላህ መልዕክተኛም ሲመልሱ እንዲህ አሉ “ኢስላም ከአላህ በስተቀር መመለክ የሚገባው እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ እንደሆነ መመስከር፣ ሰላትን ቀጥ አድርገህ መስገድ፣ ዘካትን መስጠት፣ የረመዳንን ወር መፆምና ከቻልክ በይትን ሀጅ ማድረግ ነው” አሉት፡፡ እሱም “እውነት ተናገርክ” አላቸው፡፡ ጠያቂ ሆኖ እውነቶት ነው ማለቱ አስገረመን፡፡ በመቀጠልም ስለኢማን ንገሩኝ? ሲላቸው እንዲ በማለት መለሱ “በአላህ ማመን እንዲሁም በመላዕክቱ፣ በመፅሐፍቱ፣ በመልዕክተኞቹ፣ በመጨረሻይቱ ቀንና ይክፋም ይልማም በውሳኔው (ቀደር) ማመን ነው” አሉ፡፡ እሱም “እውነቶን ነው” አለ፡፡ ቀጥሎም ስለ ኢህሳን[1] ንገሩኝ ሲላቸው እንዲህ አሉት “አላህን ስታመልክ ልክ እንደምታየው ሁን ባታየው እንኳን እሱ ያይሃል” ቀጥሎም ስለ ትንሳኤው ቀን (መች እንደሚከሰት) ንገሩኝ ሲላቸውም “ተጠያቂው ከጠያቂው የበለጠ ስለእሷ አያውቅም” አሉት “እሺ ስለምልክቶቿ ንገሩኝ” ሲልም “ሴት ባሪያ ጌታዋን መውለዷ ጫማና ልብስ የሌለው የታረዘ እረኛ በግንባታ መፎካከራቸው ምልክቶቿ ናቸው” አሉት፡፡ ከዚያም ተጓዘና ከቆይታ በኃላ “ዑመር ሆይ ጠያቂው ማን እንደሆነ ታውቃለህን?” ሲሉኝ “አላህና መልዕክተኛው ያውቃሉ” አልኳቸው እሳቸውም እሱ ጂብሪል ነበር ወደእናንተ የመጣውም ሃይማኖታችሁን ሊያስተምራችሁ ነበር፡፡” አሉኝ[2]

ይህ ሀዲስ የሃይማኖትን ማዕዘናትና ደረጃዎችን ያካተተ ትልቅ ሀዲስ ሲሆን በመላእክ ምርጥ መልዕክተኛ ጂብሪልና በሰው ምርጥ መልዕክተኛ ሙሐመድ ሰዐወ መካከል በውይይት መልኩ የቀረበ የላቀ የአስተምህሮ ዘዴን የያዘ ሀዲስ በመሆኑ ሙስሊሞች የአስተምህሮ ዘዴንም ሊማሩበት ይገባል፡፡

ይህ ሀዲስ መላእኮች ማመን የኢማን መሰረት መሆኑን ያካተተ ሲሆን ርዕሳችንም ይኸው ነው፡፡

በመላኢኮች የማመን ሁኔታ

በመላእኮች ማመን ብዙ ነገሮችን የሚያካትት በመሆኑ አንድ ሰው በመላእኮች በሚገባው መልኩ እንዲያውም እነዚህን ማወቅ ያስፈልገዋል፡፡

  1. እንዳሉ በእርግጠኝነት ማመን
  2. እጅግ የበዙና ቅጥራቸው ከአላህ ሌላ ማንም ሊያውቅ እንደማይችል ማመን፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል

{ وَمَا يَعْلَمُ جُنُودَ رَبِّكَ إِلَّا هُوَ } (المدثر : 31)

‹‹የጌታህንም ሰራዊት (ልክ) ከርሱ በቀር ማንም አያውቅም፡፡›› ሙደሲር 31

ቡኻሪና ሙስሊም ማሊክ ኢብን ሰዕሰዓን ጠቅሰው በዘገቡት ረዥሙ የኢስራእ ሀዲስ ላይ ነብዩ ሰዐወ እንዲህ ብለዋል

 « ثم رفع لي البيت المعمور ، فقلت : يا جبريل ! ما هذا ؟ قال : هذا البيت المعمور . يدخله كل يوم سبعون ألف ملك ، إذا خرجوا منه لم يعودوا فيه آخر ما عليهم »

“በይተል መዕሙር ተገለፀልኝና ለጅብሪል ይህ ምንድ ነው? ብዬ ጠየቅኩት እሱም ይህ በይተል መዕሙር ነው በየእለቱ ሰባ ሺህ መላእክት ገብተው ይወጡና ደግሞ ለመግባት እስከመጨረሻው ቀን አይደርሳቸውም” አሉኝ፡፡[3]

ሙስሊም አብደላህ ኢብን መስዑድን በመጥቀስ በአስተላለፉትም ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ አንዲህ ብለዋል

« يؤتى بجهنم يومئذ لها سبعون ألف زمام ، مع كل زمام سبعون ألف ملك يجرونها » صحيح مسلم برقم (2842)

“የዛን እለት ጀሀነም ሰባ ሺህ ልጓም ኖሯት ትመጣለች እያንዳንዱም ልጓም ሰባ ሺህ መላእክት ይዘወ ይጎትታሉ፡፡”[4]

እነዚህ ሁለት ሀዲሶች የመላኢኮች ቁጥር በጣም ብዙ መሆኑን ይጠቁማሉ ምክንያቱም በይተል መዕሙር በየእለቱ ሰባ ሺህ መላእክት ገብተው ዳግም የመመለስ እድልን ማያገኙና ጀሀነምን የሚጎትቱ መላእኮች ይህን ያልህ ብዛት ካላቸው የተቀሩት በሌሎች ኃላፊነቶች ላይ የተመደቡ መላእኮች ብዛት ሰፍና ቁጥራቸው ከአላህ ሌላ ሊያውቃቸው የሚሳን ብዛት አላቸው ማለት ነው፡፡

  1. ጌታቸው ዘንድ ከፍተኛ ማዕረግና የላቀ ደረጃ እንዳላቸው ማመን፡፡ አላህ እንዲህ ይላል

{ وَقَالُوا اتَّخَذَ الرَّحْمَنُ وَلَدًا سُبْحَانَهُ بَلْ عِبَادٌ مُكْرَمُونَ }{ لَا يَسْبِقُونَهُ بِالْقَوْلِ وَهُمْ بِأَمْرِهِ يَعْمَلُونَ } (الأنبياء : 26 ، 27)

«አልረሕማንም (ከመላእክት) ልጅን ያዘ» አሉ፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም (መላእክት) የተከበሩ ባሮች ናቸው፡፡  በንግግር አይቀድሙትም፤ (ያላለውን አይሉም)፡፡ እነርሱም በትእዛዙ ይሠራሉ፡፡›› አል አንቢያህ 26-27

{ بِأَيْدِي سَفَرَةٍ }{ كِرَامٍ بَرَرَةٍ } (عبس : 15 ، 16)

‹‹በጸሐፊዎቹ (መላእክት) እጆች (ንጹሕ የተደረገች)፡፡ የተከበሩና ታዛዦች በኾኑት (ጸሐፊዎች እጆች)፡፡››  ዓበሰ 15-16

እንዲህ ሲልም እርሱ ዘንድ የመሆናቸውን ክብርና ያለመሰልቸት አምላኪዎች መሆናቸውን ይገልፃል፡፡

{فَالَّذِينَ عِنْدَ رَبِّكَ يُسَبِّحُونَ لَهُ بِاللَّيْلِ وَالنَّهَارِ وَهُمْ لَا يَسْأَمُونَ } (فصلت : 38)

‹‹እነዚያ በጌታህ ዘንድ ያሉት (መላእክት) በቀንም በሌሊትም ለእርሱ ያወድሳሉ፡፡ እነርሱም አይሰለቹም፡፡›› ፉሲለት 38

እርሱ ዘንድ ያላቸው ክብር ከፍ ያለ በመሆኑም በቁርአን በተለያዩ ቦታዎች በነሱ ይምላል

{ وَالصَّافَّاتِ صَفًّا }{ فَالزَّاجِرَاتِ زَجْرًا }{ فَالتَّالِيَاتِ ذِكْرًا } (الصافات : 1-3)

‹‹መሰለፍን በሚሰለፉት፡፡ መገሠጽንም በሚገሥጹት፤ ቁርኣንንም በሚያነቡት እምላለሁ፡፡›› ሷፋት 1-3

{ فَالْفَارِقَاتِ فَرْقًا }{ فَالْمُلْقِيَاتِ ذِكْرًا } (المرسلات : 4 ، 5)

‹‹መለየትን ለይዎች በኾኑትም፣ መገሠጫን (ወደ ነቢያት) ጣይዎች በኾኑትም›› ሙርሰላት 4-5

ቁርአን ላይ የመላኢኮችን ክብር የተለያዩ ሁኔታዎት የሚያብራሩ አንቀፆች ብዙ በመሆናቸው ቁርአንን ላስተዋለ ሰው አይደሉም፡፡

  1. ማዕረጎቻቸው እንደሚለያዩና አንዱ ከሌላው እንደሚበላለጥ ማመን፡፡

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የተለያዩ አንድ ከሌላው የሚበላለጡባቸው ማዕረጎች አሏቸው፡፡ አላህ አንዲህ ይላል

{ اللَّهُ يَصْطَفِي مِنَ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا وَمِنَ النَّاسِ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ بَصِيرٌ } (الحج : 75)

‹‹አላህ ከመላእክት ውስጥ መልክተኞችን ይመርጣል፡፡ ከሰዎችም (እንደዚሁ) አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡››  አል ሀጅ 75

{ لَنْ يَسْتَنْكِفَ الْمَسِيحُ أَنْ يَكُونَ عَبْدًا لِلَّهِ وَلَا الْمَلَائِكَةُ الْمُقَرَّبُونَ } (النساء : 172)

‹‹አልመሲሕ (ኢየሱስ) ለአላህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ ቀራቢዎች የኾኑት መላእክትም (አይጠየፉም)፡፡›› አል ኒሳእ 172

ከመላኢኮች በማዕረግ በላጮች ወደ አላህ ቅርቦችና ዐርሽን ተሸካሚዎች ሲሆኑ ከነሱም ውስጥ ምርጦች ነብዩ ሰዐወ የሌሊትን ሰላት የሚከፍቱበት ዱዓ ውስጥ የተካተቱ ሶስት መላእክቶች ናቸው፡፡ ዱዓቸው ላይ እንዲህ ይሉ ነበር

« اللهم رب جبريل وميكائيل وإسرافيل فاطر السماوات والأرض عالم الغيب والشهادة » . . ) 

“አላህ ሆይ የጂብሪል የሚካኤልና የኢስራፌል ጌታ፣ ሰማያትና ምድርን ፈሪ፣ ስውርንም ግልፅንም አዋቂ…”

ከሶስቱ ምርጥ ደግሞ ወህይን እንዲያስተላለፍ የተመደበው ጂብሪል ሲሆን የርሱም ክብር ከተመደበበት ኃላፊነት ትልቀት የተነሳ ነው፡፡ አላህ በቁርአኑ ሌሎች መላእክቶችን ከጠቀሰበት በተለየ መልኩ የጠቀሰው ሲሆንን በተከበረ ስያሜውና ባማረ ባህሪው ገልፆታል፡፡ ከተሰየመበት ስያሜ አንዱ “መንፈስ” ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል

{ نَزَلَ بِهِ الرُّوحُ الْأَمِينُ } (الشعراء : 193)

‹‹እርሱን ታማኙ መንፈስ (ጂብሪል) አወረደው›› ሹዓራእ 193

{ تَنَزَّلُ الْمَلَائِكَةُ وَالرُّوحُ فِيهَا } (القدر : 4)

‹‹በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡››  አል ቀደር 4

ይህ ስም ከአላህ ጋር በክብር ተዛምዶ ተጠቅሷል

{ فَأَرْسَلْنَا إِلَيْهَا رُوحَنَا فَتَمَثَّلَ لَهَا بَشَرًا سَوِيًّا } (مريم : 17)

‹‹መንፈሳችንምም (ጂብሪልን) ወደርሷ ላክን፡፡ ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡›› መርየም 17

ከቅዱስ ጋር ተቆራኝቶም ተጠቅሷል

{ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِنْ رَبِّكَ } (النحل : 102)

‹‹(ቁርኣንን) ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው በላቸው፡፡›› አል ነህል 1ዐ2

ጅብሪል ከተገለፁበት ሌሎች ባህሪያት ደግሞ ክቡር፣ ሀያል፣ ጌታው ዘንድ ባለማዕረግ፣ ሰማያት ላይ ትዕዛዙ ተሰሚ፣ ወህይን በማስተላለፍ ታማኝ፣ ውብ ይገኙበታል፡፡

{ إِنَّهُ لَقَوْلُ رَسُولٍ كَرِيمٍ }{ ذِي قُوَّةٍ عِنْدَ ذِي الْعَرْشِ مَكِينٍ }{ مُطَاعٍ ثَمَّ أَمِينٍ } (التكوير : 19- 21)

‹‹እርሱ (ቁርኣን) የክቡር መልክተኛ ቃል ነው፡፡ የኀይል ባለቤት በዙፋኑ ባለ ቤት ዘንድ ባለሟል የኾነ፡፡ በዚያ ስፍራ ትእዛዙ ተሰሚ፤ ታማኝ የኾነ (መልክተኛ ቃል) ነው፡፡›› ተክዊር 19-21

{ عَلَّمَهُ شَدِيدُ الْقُوَى }{ ذُو مِرَّةٍ فَاسْتَوَى } (النجم : 5 ، 6)

‹‹ኀይሎቹ ብርቱው (መልአክ) አስተማረው፡፡ የዕውቀት ባለቤት የኾነው (አስተማረው፤ በተፈጥሮ ቅርጹ ኾኖ በአየር ላይ) ተደላደለም፡፡›› አል ነጅም 5-6

  1. እነሱን መወዳጀት እነሱን ከመጥላት መጠንቀቅ፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል

{ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ } (التوبة : 71)

‹‹ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡›› አል ተውባህ 71

መልአኮች አላህ ስለነሱ ሲናገር

{ لَا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ } (التحريم : 6)

‹‹አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡›› ተህሪም 6

እንዳለው ታዛዦችና አማኞች በመሆናቸው በዚህ አንቀፅ ውስጥ ይካተታሉ፡፡

መልአኮች በሚከተሉት አንቀፆች እንደተነገረው መልዕክተኞችንና ምእመናንን ወዳጆች ረዳቶችና ለነሱም ምህረትን ጠያቂዎች በመሆናቸው እነሱንም መውደድና ወዳጅ ማድረግ ግድ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል

{ وَإِنْ تَظَاهَرَا عَلَيْهِ فَإِنَّ اللَّهَ هُوَ مَوْلَاهُ وَجِبْرِيلُ وَصَالِحُ الْمُؤْمِنِينَ } (التحريمَ : 4)

‹‹በእርሱም ላይ ብትረዳዱ አላህ እርሱ ረዳቱ ነው፡፡ ጂብሪልም ከምእምናንም መልካሙ ከዚህም በኋላ መላእክቱ ረዳቶቹ ናቸው፡፡›› ተህሪም 4

{ هُوَ الَّذِي يُصَلِّي عَلَيْكُمْ وَمَلَائِكَتُهُ لِيُخْرِجَكُمْ مِنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ } (الأحزاب : 43)

‹‹እርሱ በእናንተ ላይ እዝነትን የሚያወርድ ነው፡፡ መላእክቶቹም (እንደዚሁ ምሕረትን የሚለምኑላችሁ ናቸው)፡፡ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣችሁ ዘንድ (ያዝንላችኋል)፡፡ አል አህዛብ 43

{ إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا } (فصلتَ : 30)

እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ «አትፍሩ፤ አትዘኑም … ›› በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡ ፉሲለት 3ዐ

በአንፃሩም መላእክቶችን ጠላት ማድረግን አላህ እንዲህ ሲል አስጠንቅቋል፡፡

{ مَنْ كَانَ عَدُوًّا لِلَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَرُسُلِهِ وَجِبْرِيلَ وَمِيكَالَ فَإِنَّ اللَّهَ عَدُوٌّ لِلْكَافِرِينَ }(البقرة : 98)

‹‹ለአላህና ለመላእክቱ ለመልክተኞቹም ለጂብሪልም ለሚካልም (ሚካኤል) ጠላት የኾነ ሰው አላህ (እነዚህ) ከሓዲዎች ጠላት ነው፡፡›› አል በቀራህ 98

በአላህ ትዕዛዝ በርሱ ፍርዱ ተንቀሳቃሽ በመሆናቸው እነሱን መጥላት ጌታቸውን መጥላት ስለሆነ ለነሱ ጠላት መሆን የአላህን ጥላቻ እንደሚያስከትል ገለፀ፡፡

  1. መልአኮች አላህ ከፈጠራቸው ፍጡሮች የሚመደቡ እንጂ በመፍጠርም በማከናወንም ሆነ በማስተናበር ድርሻ እንደሌላቸው እንዲያውም በአላህ ትዕዛዝ የሚሰሩ የርሱ ሰራዊቶች ይሁኑ እንጂ ነገሩ ሁሉ አጋር በሌለው አላህ ቁጥጥር ስር መሆኑን ማመን፡፡ እንዲሁም ደግሞ ምንም አይነት አምልኮ ለነሱ ማድረግ የማይፈቀድና አምልኮዎች በአጠቃላይ የነሱና የሌሎች ፍጡራን ሁሉ ፈጣሪ ለሆነው አላህ ብቻ እንደሚገባ ማመን፡፡

ይህንን አላህ ሲያብራራ እንዲህ ይላል

{ وَلَا يَأْمُرَكُمْ أَنْ تَتَّخِذُوا الْمَلَائِكَةَ وَالنَّبِيِّينَ أَرْبَابًا أَيَأْمُرُكُمْ بِالْكُفْرِ بَعْدَ إِذْ أَنْتُمْ مُسْلِمُونَ } (آل عمران : 80)

‹‹መላእክትንና ነቢያትንም አማልክቶች አድርጋችሁ እንድትይዙ ሊያዛችሁ (አይገባውም)፡፡ እናንተ ሙስሊሞች ከኾናችሁ በኋላ በክህደት ያዛችኋልን?›› አል ዒምራን 8ዐ

{ وَقَالُوا اتَّخَذَ الرَّحْمَنُ وَلَدًا سُبْحَانَهُ بَلْ عِبَادٌ مُكْرَمُونَ }{ لَا يَسْبِقُونَهُ بِالْقَوْلِ وَهُمْ بِأَمْرِهِ يَعْمَلُونَ }{ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ارْتَضَى وَهُمْ مِنْ خَشْيَتِهِ مُشْفِقُونَ }{ وَمَنْ يَقُلْ مِنْهُمْ إِنِّي إِلَهٌ مِنْ دُونِهِ فَذَلِكَ نَجْزِيهِ جَهَنَّمَ كَذَلِكَ نَجْزِي الظَّالِمِينَ } (الأنبياء : 26-29)

«አልረሕማንም (ከመላእክት) ልጅን ያዘ» አሉ፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም (መላእክት) የተከበሩ ባሮች ናቸው፡፡  በንግግር አይቀድሙትም፤ (ያላለውን አይሉም)፡፡ እነርሱም በትእዛዙ ይሠራሉ፡፡ በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡ ከእነሱም «እኔ ከእርሱ ሌላ አምላክ ነኝ» የሚል ያንን ገሀነምን እንመነዳዋለን፡፡ እንደዚሁ በዳዮችን እንመነዳለን፡፡›› አል አንቢያህ 26-29

  1. አንዳንድ ስማቸው ወይም ባህሪያቸው በቁርአንና ሀዲስ በተጠቀሱ መላእኮች በእያንዳንዱ ተናጥል የሆነ ኢማን ማመን፡፡

በስሞቻቸው ከተጠቀሱ መላእኮች ለምሳሌ ጂብሪል፣ ሚካኤል፣ ኢስራኤል፣ ማሊክ፣ ሃሩት፣ ማሩት፣ ሪድዋን፣ ሙንከርና ነኪር፡፡ በባህሪያቸው ከተጠቀሱ ውስጥ ለምሳሌ በረቂብና ዓቲድ በስራ ኃላፊነታቸው ከተጠሩ ውስጥ ለምሳሌ በመለኩል መውት፣ የተራሮች መልአክ፣ የዐርሽ ተሸካሚዎች፣ የተከበሩ ፀሐፊዎች፣ ሰዎችን ጠባቂዎች፣ ፅንሶችንና ማህፀኖችን ተቆጣጣሪዎች፣ በተይተል መዕሙርን ጠዋፍ አድራጊዎች፣ ምድር ላይ ተጓጓዦች እና ሌሎችም በቁርአንና በሀዲስ በተዘረዘሩ መላእክቶችና በሚቀጥለው ጥናት ውስጥ በሚዘረዘሩ ኃላፊነቶችና ስራዎች በእያንዳንዱ በተናጥል ማመን ግዴታ ነው፡፡

[1] ኢህሳን ……….

[2] ሙስሊም 8

[3] ቡኻሪ 32ዐ2

[4] ሙስሊም 2842