‹ሙሐመዱን ረሱሉላህ› የሚለው የምስክርነት ቃል መስፈርቶች…

0
235

ሙሐመዱን ረሱሉላህ› የሚለው የምስክርነት ቃል መስፈርቶች እና የነብያችን صلى الله عليه وسلم ዉዴታ መገለጫዎች 

  1. ነብያችን صلى الله عليه وسلم  የአላህ ነብይና ረሱል መሆናቸውን ማመን እና በአንደበትም መመስከር፡፡
﴿يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ شَاهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا (45) وَدَاعِيًا إِلَى اللَّهِ بِإِذْنِهِ وَسِرَاجًا مُنِيرًا (46) وَبَشِّرِ الْمُؤْمِنِينَ بِأَنَّ لَهُمْ مِنَ اللَّهِ فَضْلًا كَبِيرًا (47) ﴾ اللأحزاب 45-47

“አንተ ነብዩ ሆይ እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን ላክንህ፤ ወደ አላህም በፈቃዱ ጠሪ፣ አብሪ ብርሃንም (አድርገን ላክንህ) ፤ አማኞችንም ከአላህ ዘንድ ለእነርሱ ታላቅ ችሮታ ያላቸው መሆኑን አበስራቸው”  አል አህዛብ 45-47

  1. ነብያችን صلى الله عليه وسلم የተላኩበትን መልዕክት በሚገባ መልኩ ማድረሳቸውንና ማስተላለፋቸውን እና አደራቸውን መወጣታቸውን ማመንና መመስከር፡፡
﴿يَأْمُرُهُمْ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَاهُمْ عَنِ الْمُنْكَرِ وَيُحِلُّ لَهُمُ الطَّيِّبَاتِ وَيُحَرِّمُ عَلَيْهِمُ الْخَبَائِثَ وَيَضَعُ عَنْهُمْ إِصْرَهُمْ وَالْأَغْلَالَ الَّتِي كَانَتْ عَلَيْهِمْ﴾ الأعراف 157

“… በበጎ ስራ ያዛቸዋል ከክፉም ነገር ይከለክላቸዋል መልካም ነገሮችንም ለነርሱ ይፈቅድላቸዋል መጥፎ ነገሮችንም በነርሱ ላይ እርም ያደርግላቸዋል፡፡ ከነሱም ላይ ሸክማቸውንና እነዚያንም በነሱ ላይ የነበሩትን እንዛዝላዎች (ከባድ ሕግጋቶች) ያነሳላቸዋል፡” አል አዕራፍ 157

  1. ነብያችንን صلى الله عليه وسلم  ከራስ፣ከገንዘብ፣ከልጆችና ከወላጆች አንዲሁም ከሰው ልጆች ሁሉ አስበልጦ መውደድ፡፡ ይህም ፈለጋቸዉን በመከተል እና በመተግበር ይገለፃል፡፡
عن أَنَسٍ – رضي الله عنه – قال: قال النبي – صلى الله عليه وسلم – : »لا يُؤْمِنُ أحدكم حتى أَكُونَ أَحَبَّ إليه من وَالدِهِ وَوَلدِهِ وَالنَّاسِ أَجْمَعِينَ«  رواه البخاري ومسلم
‹‹ከወላጁ፣ ከልጁ፣ ከሰው ሁሉ ይበልጥ እርሱ ዘንድ ተወዳጅ እስካልሆንኩ ድረስ አንዳችሁም አላመነም›› [1]
  1. ነበያችን صلى الله عليه وسلم ያዘዙትን ሁሉ መውደድ የከለከሉትን ነገር ሁሉ መጥላትና መራቅ፤

﴿وَمَا كَانَ لِمُؤْمِنٍ وَلَا مُؤْمِنَةٍ إِذَا قَضَى اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَمْرًا أَنْ يَكُونَ لَهُمُ الْخِيَرَةُ مِنْ أَمْرِهِمْ وَمَنْ يَعْصِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا مُبِينًا﴾ الأحزاب 36

“አላህና መልክተኛው በአንድ ነገር ላይ ነገር በፈረዱ ጊዜ ምእመናንና ምዕመናት ከዚያ የተለየ ምርጫ ሊኖራቸው አይገባም፡፡ አላህንና መልዕክተኛዉን ያልታዘዘ ግልጽ ጥመትን በርግጥ ጠሟል” አል አህዛብ 36

عن أبي أمامة مرفوعا »من أحب لله وأبغض لله وأعطى لله ومنع لله فقد استكمل الايمان « رواه أبو داود

«ነብያችን እንዲህ ብለዋል “ለአላህ ብሎ የወደደ ለአላህ ብሎ የጠላ ለአላህ ብሎ የሰጠ ለአላህ ብሎ የከለከለ በእርግጥ እምነቱ ሞላ፡፡»[2]

  1. ነብያችንን صلى الله عليه وسلم በትንሽም ይሁን በትልቅ ነገር ላይ መከተልና መታዘዝ ፈለጋቸውን መውረስ። የከለከሉትንና ያስጠነቀቁትን ነገር መራቅና መተው፡፡

﴿ قُلْ أَطِيعُوا اللَّهَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ فَإِنْ تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا عَلَيْهِ مَا حُمِّلَ وَعَلَيْكُمْ مَا حُمِّلْتُمْ وَإِنْ تُطِيعُوهُ تَهْتَدُوا وَمَا عَلَى الرَّسُولِ إِلَّا الْبَلَاغُ الْمُبِينُ ﴾ النور 54

“አላህን ታዘዙ መልዕክተኛውንም ታዘዙ፤ ግን ብትሸሹ (አትጎዱትም)፤ በእርሱ ላይ ያለበት የተሸከመዉን (ሀላፊነት) ማድረስ ብቻ ነው፤ በእናንተ ላይ ያለባችሁ ሀላፊነትም (መታዘዝ) ብቻ ነው፤ ብትታዘዙትም ቅኑን ጎዳና ትመራላችሁ። በመልዕክተኛው ላይ ግልፅ ማድረስ እንጅ ሌላ የለበትም፤ በላቸው፡፡” አል ኑር 54

﴿ وَمَا آَتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانْتَهُوا وَاتَّقُوا اللَّهَ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ﴾ الحشر 7

“መልዕክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት ከርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ አላህንም ፍሩ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡” አል ሐሽር 7

﴿ مَنْ يُطِعِ الرَّسُولَ فَقَدْ أَطَاعَ اللَّهَ وَمَنْ تَوَلَّى فَمَا أَرْسَلْنَاكَ عَلَيْهِمْ حَفِيظًا ﴾ النساء 80

“መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ የሸሸ ሰው በነሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህም፡፡” ኒሳእ 8ዐ

﴿ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمَنُوا اسْتَجِيبُوا لِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ إِذَا دَعَاكُمْ لِمَا يُحْيِيكُمْ وَاعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ يَحُولُ بَيْنَ الْمَرْءِ وَقَلْبِهِ وَأَنَّهُ إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ ﴾ الأنفال 24

“…እናንተ ያመናችሁ ሆይ (መልዕክተኛው) ሕያው ወደሚያደርጋችሁ እምነት በጠራችሁ ጊዜ ለአላህና ለመልዕክተኛው ታዘዙ አላህም በሰውየውና በልቡ መካከል የሚጋርድ መሆኑን ወደርሱም የምትሰበስቡ መሆናችሁን እወቁ፡፡” አል አንፋል 24

  1. ከዚህ በፊት ተከስተው ስለማለፋቸውም ይሁን ወደፊት ስለመከሰታቸው በመልእክተኛው ع የተነገሩ ነገሮችን እውነት መሆናቸውን አምኖ መቀበል፡፡

﴿وَمَا يَنْطِقُ عَنِ الْهَوَى ﴾ النجم 3

“ከልብ ወለድ አይናገርም እርሱ (ቁርአን) ከአላህ የተወረደለት እንጅ ሌላ አይደለም፡፡” አል ነጅም 3

  1. የአላህንና የመልእክተኛው صلى الله عليه وسلم ንግግር ከማንም ንግግር ማስበለጥ፡፡

﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمَنُوا لَا تُقَدِّمُوا بَيْنَ يَدَيِ اللَّهِ وَرَسُولِهِ وَاتَّقُوا اللَّهَ إِنَّ اللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ﴾ الحجرات 1

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ ከአላህና ከመልዕክተኛው ፊት (ነፍሶቻችሁን) አታስቀድሙ አላህንም ፍሩ አላህ ሰሚ አዋቂ ነውና፡፡” አል ሁጅራት 1

ይህንን አንቀጽ አስመልክቶ ኢብኑል ቀይም እንዲህ ብለዋል፤

ነብዩع እስካልተናገሩ ድረስ አትናገሩ፤እስካላዘዙ ድረስ አትዘዙ፤ ብይን እስካልሰጡ ድረስ ብይን አትስጡ፤እሳቸው እስካልወሰኑበትና እስካላፀደቁት ድረስ በአንድ ነገር ላይ ውሳኔ አታሳልፉ፤ የሚለዉን ሁሉ ያካትታል[3]

ስለዚህ እሳቸው ያላፀደቁትን ነገር በዲናችን ላይ ማፅደቅ፤ የዲናችን አንድ ክፍል አድርገን ማየት፤ በጭራሽ የማይደገፍ መሆኑን እንረዳለን፡፡

﴿ بِالْبَيِّنَاتِ وَالزُّبُرِ وَأَنْزَلْنَا إِلَيْكَ الذِّكْرَ لِتُبَيِّنَ لِلنَّاسِ مَا نُزِّلَ إِلَيْهِمْ وَلَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ ﴾ النحل 44

“በግልፅ ማስረጃዎችና በመፃህፍት (ላክናቸው)፤ ወደ አንተም ለሰዎች ወደነሱ የተወረደውን (ፍች) ልትገልፅላቸውና ያስተነትኑም ዘንድ ቁርአንን አወረድን፡፡” አል ነህል 44

ነብያችን صلى الله عليه وسلم  ባልደነገጉትና ባልፈቀዱት መልኩ አላህን አለመገዛት (አለማምለክ)፡፡ ነብያችን ع እንዲህ ብለዋል፤

قال النَّبِيِّ ع »مَنْ عَمِلَ عَمَلًا لَيْسَ عَلَيْهِ أَمْرُنَا فَهُوَ رَدٌّ« رواه البخاري ومسلم

«የእኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ (ስራው) ተመላሽ ነው (ተቀባይነት የለውም)»[4]

  1. ወደ ረሱል صلى الله عليه وسلم  ፍርድ መፋረድና ፍርዱንና ውሳኔውን ወደህ መቀበል፤

﴿ فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّى يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا فِي أَنْفُسِهِمْ حَرَجًا مِمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾ النساء 65

“በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍፁም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም፡፡” አል ኒሳእ 65
  1. እሳቸውን በብዛት ማውሳትና በእሳቸው ላይ ሰለዋት ማውረድ

﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا﴾ الأحزاب 56

“አላህና መላእክቱ በነብዩ ع ላይ “ሶለዋት ያወርዳሉ” (ምህረትን ይለምናሉ)፤ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በርሱ ላይ ሰለዋትን አውርዱ ፤ የማክበርንም ሰላምታንም አቅርቡለት” አል አህዛብ 56

  1. ነብዩን (صلى الله عليه وسلم) በተመለከተ የሚነሱ መጥፎ ትችቶችንና ንግግሮችን መከላከል፤ የእርሳቸውን ክብር የሚነኩና እሳቸውን የሚያንቋሽሹ ሰዎችን መታገል፡፡

ነብዩ  በእሁድ ዘመቻ እንዲህ ብለዋል፤ “ከኛ ላይ የሚመልሳቸው (የሚመክታቸው) ለሱ ጀነት አለው፡፡”

﴿ وَلَيَنْصُرَنَّ اللَّهُ مَنْ يَنْصُرُهُ إِنَّ اللَّهَ لَقَوِيٌّ عَزِيزٌ ﴾ الحج 40

“አላህም (ሃይማኖቱን) የሚረዳውን ሰው በእርግጥ ይረዳዋል አላህ ብርቱ አሸናፊ ነው፡፡” አል ሐጅ 4ዐ

﴿ إِنَّا لَنَنْصُرُ رُسُلَنَا وَالَّذِينَ آَمَنُوا فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَيَوْمَ يَقُومُ الْأَشْهَادُ ﴾ غافر 51
“እኛ መልዕክተኞቻችንን እነዚያንም ያመኑትን በቅርቢቱ ህይወት ምስክሮችም በሚቆሙበት ቀን በእርግጥ እንረዳለን፡፡” ጋፊር 51
  1. የነብዩን صلى الله عليه وسلم የህይወት ታሪክ በብዛት ማንበብ እና መተዋወስ፡፡ከእርሳቸው ጋር ለመገናኘት መናፈቅ፡፡
  2. በተገቢው መልኩ የነብዩን صلى الله عليه وسلم ቤተሰቦች እና ባልደረቦች መውደድ ፣ ማላቅና ማክበር፡፡

[1] ቡኻሪና ሙስሊም ከአነስ ኢብኑ ማሊክ ዘግበውታል

[2] አቡ ዳውድ በሐዲስ ቁጥር 4681 ዘግበዉታል ሸይህ አልባኒም ሰሂህነቱን አረጋግጠዋል

[3] ኢብኑልቀይም (ኢዕላሙል ሙወቂዒን አን ረቢልዓለሚን) ቅጽ 1 ገጽ 51

[4] ቡኻሪ በቁጥር 1718 እና ሙስሊም በቁጥር 2550 ዘግበውታል