ለወላጆች መልካምን መዋል

0
287

  ?   بر الوالدين   ?

በታላቁ ፈቂህ አል-ዐል’ላማ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ)

? ባሁኑ ወቅት ያለውን የሰዉን ሁኔታ ካስተዋልነው በርካታ ሰዎች ለወላጆቻቸው መልካም እንደማይውሉ ሆነው እናገኛለን። እንዲያውም ለወላጆቻቸው መብት ነፋጊ እንደሆኑ ነው የምንረዳው።

  በዚህም ለጓደኞቹ መልካምን ሲውል ታገኘዋለህ። ከነሱ ጋር ሲቀመጥ (ሲጨዋወት) አይሰለቸውምና። ነገር ግን ከአባቱ ወይም ከእናቱ ጋር አንዲት ሰዓት እንኳ ቢቀመጥ ልክ ፍም እሳት ላይ የተቀመጠ እስኪመስል ተጨናንቆ ሲገላበጥ ታገኘዋለህ።

  ይህ አይነቱ ሰው ለወላጆች መልካም ዋይ አይሆንም።

  ለወላጆች መልካም የሚውል ሰውማ ለናቱና ላባቱ ልቡን ክፍት ያደርጋል። ልክ እንዳይኖቹ ቅንድብ ይንከባከባቸዋል። በሚችለው ሁሉ እነሱን ለማስደሰት ይጓጓል።?

【ሸርህ ዐቂደቱል ዋሲጢያ: 3/121】

ጀሪር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳወራልን የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ጨረቃ ሙሉ ሆና ቦግ ባለችበት የወሩ አጋማሽ ሌሊት (ለይለቱል በድር) ወደ ውጭ ወጡና እንዲህ ኣሉን☞

« ልክ ይህንን መመልከታችሁ እንደማይታበል ሁሉ፤ እናንተ ጌታችሁን የቂያም እለት ታዩታላችሁ። »

【ቡኻሪ ዘግበውታል】