በመፃህፍት የማመን ሁኔታ

0
400

ይህን የላቀ የእምነት ማዕዘን ለማረጋገ የሚያስችሉ የተለያዩ በመፅሐፍ ላይ የማመን አቅጣጫዎች አሉ፡፡

  1. ከአላህ ዘንድ የተወረዱና በራሱ ንግግር በመናገር ያስተላለፋቸው መሆናቸውን በእርግጠኝነት ማመን፡፡ አላህ እንዲህ ይላል

{ اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ }{ نَزَّلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنْزَلَ التَّوْرَاةَ وَالْإِنْجِيلَ }{ مِنْ قَبْلُ هُدًى لِلنَّاسِ وَأَنْزَلَ الْفُرْقَانَ إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِآيَاتِ اللَّهِ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَاللَّهُ عَزِيزٌ ذُو انْتِقَامٍ } (آل عمران : 2- 4)

‹‹አላህ ከርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ (እርሱ) ሕያው ሁሉን ነገር አስተናባሪ ነው፡፡ ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን (ቁርኣንን) ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል፡፡ (ከቁርኣን) በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ (አወረዳቸው)፡፡ ፉርቃንንም አወረደ፡፡ እነዚያ በአላህ ተዓምራቶች የካዱ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው፡፡ አላህም አሸናፊ የመበቀል ባለቤት ነው፡፡›› አል ዒምራን 2-4

እዚህ ላይ የተጠቀሱ መፃህፍት ማለትም ተውራት ኢንጂል ቁርአን ከርሱ ዘንድ መሆኑን መግለፁ የእርሱ ራሱ ንግግር እንጂ የሌላ እንዳልሆነ ያሳያል፡፡ ስለተውራት ሲናገርም እንዲህ ብሏል

{ إِنَّا أَنْزَلْنَا التَّوْرَاةَ فِيهَا هُدًى وَنُورٌ } (المائدة : 44)

‹‹እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትኾን አወረድን፡፡›› አል ማኢዳህ 44

ተውራት ያወረደው እራሱ እንደሆነና በውስጧ ያሉ መመሪያና ብርሃንም ከርሱ ዘንድ መሆኑን በግልፁ አስቀመጠ፡፡ ስለ የሁዶች እየተናገረ ባለበት አጋጣሚም ተውራት የርሱ ንግግር እንደሆነ እንዲህ ሲል ይናገራል፡፡

{ أَفَتَطْمَعُونَ أَنْ يُؤْمِنُوا لَكُمْ وَقَدْ كَانَ فَرِيقٌ مِنْهُمْ يَسْمَعُونَ كَلَامَ اللَّهِ ثُمَّ يُحَرِّفُونَهُ مِنْ بَعْدِ مَا عَقَلُوهُ } (البقرة : 75)

‹‹(አይሁዶች) ከነሱ የኾኑ ጭፍሮች የአላህን ቃል የሚሰሙና ከዚያም ከተረዱት በኋላ እነርሱ እያወቁ የሚለውጡት ሲኾኑ ለናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን?›› አል በቀራህ 75

ሱድይ ኢብኑ ዘይድና ሌሎችም የቁርአን ትርጉም ተንታኞች እንዳሉት ከሰሙ በኃላ ትርጉሙን ያዛቡት የአላህ ንግግር ተውራት ነው፡፡

ስለኢንጂልም አላህ እንዲህ ይላል

{ وَلْيَحْكُمْ أَهْلُ الْإِنْجِيلِ بِمَا أَنْزَلَ اللَّهُ فِيهِ } (المائًدة : 47)

‹‹የኢንጅልም ባለቤቶች በውስጡ አላህ ባወረደው ሕግ ይፍረዱ፡፡›› አል ማኢዳህ 47

ማለትም ትዕዛዛትንና ክልከላን ባካተተው የአላህ ንግግር ማለት ነው፡፡

ስለቁርአንም እንዲህ ብሏል

{ الر كِتَابٌ أُحْكِمَتْ آيَاتُهُ ثُمَّ فُصِّلَتْ مِنْ لَدُنْ حَكِيمٍ خَبِيرٍ } ( هود : 1)

‹‹አ.ለ.ረ (አሊፍ ላም ራ፤ ይህ ቁርኣን) አንቀጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ጥበበኛ ውስጠ ዐዋቂ ከሆነው ዘንድ (የተወረደ) ነው፡፡››  ሁድ 1

መልዕክተኛውንም እንዲህ ሲል ያናግራል

{ وَإِنَّكَ لَتُلَقَّى الْقُرْآنَ مِنْ لَدُنْ حَكِيمٍ عَلِيمٍ } (النمل : 6)

‹‹አንተም ቁርኣንን ጥበበኛና ዐዋቂ ከኾነው (ጌታህ) ዘንድ በእርግጥ ትስሰጣለህ፡፡›› ነምል 6

{ قُلْ نَزَّلَهُ رُوحُ الْقُدُسِ مِنْ رَبِّكَ } (النحل : 102)

‹‹(ቁርኣንን) ቅዱሱ መንፈስ (ጂብሪል) እውነተኛ ሲኾን ከጌታህ አወረደው በላቸው፡፡›› አል ነህል 1ዐ2

{ وَإِنْ أَحَدٌ مِنَ الْمُشْرِكِينَ اسْتَجَارَكَ فَأَجِرْهُ حَتَّى يَسْمَعَ كَلَامَ اللَّهِ } (التوبة : 6)

‹‹ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው፡፡›› ተውባህ 6

  1. እያንዳንዱ መፃህፍት አላህ በብቸኝነት እንዲመለክ የተጣሩና መልካምን ነገር፣ መመሪያንና ብርሃንን ይዘው እንደመጡ ማመን፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል

{ مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَنْ يُؤْتِيَهُ اللَّهُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا عِبَادًا لِي مِنْ دُونِ اللَّهِ } (آل عمران : 79)

‹‹ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠውና ከዚያም ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ኾኑ» ሊል አይገባውም፡፡›› አል ዒምራን 79

መፃህፍቱ እውነትንና መመሪያን ያዘሉ መሆናቸውንም ሲገልፅ እንዲህ ይላል

{ نَزَّلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنْزَلَ التَّوْرَاةَ وَالْإِنْجِيلَ }{ مِنْ قَبْلُ هُدًى لِلنَّاسِ } (آل عمران : 3 ، 4)

‹‹ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲኾን መጽሐፉን (ቁርኣንን) ባንተ ላይ ከፋፍሎ በእውነት አወረደ፡፡ ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል፡፡ (ከቁርኣን) በፊት ለሰዎች መሪ አድርጎ (አወረዳቸው)፡፡›› ዒምራን 3-4

{ كَانَ النَّاسُ أُمَّةً وَاحِدَةً فَبَعَثَ اللَّهُ النَّبِيِّينَ مُبَشِّرِينَ وَمُنْذِرِينَ وَأَنْزَلَ مَعَهُمُ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ } (البقرة : 213)

‹‹ሰዎቹ ሁሉ አንድ ሕዝብ ነበሩ፤ (ተለያዩ)፡፡ አላህም ነቢያትን አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርጎ ላከ፡፡ ከእነርሱም ጋር መጻሕፍትን በሰዎቹ መካከል በዚያ በርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ በእውነት አወረደ፡፡›› አል በቀራህ 213

 { إِنَّا أَنْزَلْنَا التَّوْرَاةَ فِيهَا هُدًى وَنُورٌ } (المائًدة : 44)

‹‹እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትኾን አወረድን፡፡›› አል ማኢዳህ 44

{ وَآتَيْنَاهُ الْإِنْجِيلَ فِيهِ هُدًى وَنُورٌ } (المائدة : 46)

‹‹ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበትሲኾን ሰጠነው፡፡›› አል ማኢዳህ 46

{ شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنْزِلَ  فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِنَ الْهُدَى وَالْفُرْقَانِ } (البقرة : 185)

‹‹(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡›› አል በቀራህ 185

በተመሳሳይ መልኩ የአላሀ መፃህፍት ብርሃንና መመሪያን ይዘው የመጡ ማናቸውን የሚገልፁ ብዙ አንቀፆች አሉ፡፡

  1. የአላህ መፃህፍት አንዱ ለሌላው መስካሪ እንጂ አንዱ ከሌላ የሚጋጭ እንዳልሆነ ማመን፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል

{ وَأَنْزَلْنَا إِلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ الْكِتَابِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ } (المائدة : 48)

‹‹ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡›› አል ማኢዳህ 48

{ وَآتَيْنَاهُ الْإِنْجِيلَ فِيهِ هُدًى وَنُورٌ وَمُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ التَّوْرَاةِ } (المائدة : 46)

‹‹ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ… ሲኾን ሰጠነው፡፡›› አል ማኢዳህ 46

ይህ የአላህ መልዕክተኛ ከሌሎች የፍጡራን መፃህፍት የርሱ ንግግር ከሌሎች ንግግር የሚለይበት መለያ ነው፡፡ የፍጡራን ንግግር ከጉድለት ከክፍተት የማይለይ በመሆኑ አንዱ ከሌላው ጋር ይጋጫል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል

{ وَلَوْ كَانَ مِنْ عِنْدِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا } (النساء : 82)

‹‹ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡›› አል ኒሳእ 82

  1. አላህ ከመፅሐፎቹ ውስጥ በስማቸው የጠራቸውን መፃህፍት በተለየ መልኩ ከነስማቸው ማመን፡፡ ስማቸው የተጠቀሱ መፅሐፎች

ሀ. ተውራት፡- ተውራት አላህ ለሙሳ የሰጠው መፅሐፍ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል

{ وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَى الْكِتَابَ مِنْ بَعْدِ مَا أَهْلَكْنَا الْقُرُونَ الْأُولَى بَصَائِرَ لِلنَّاسِ } (القصص : 43)

‹‹የፊተኞቹን የክፍለ ዘመናት ሕዝቦችም ከአጠፋን በኋላ ለሰዎች የልብ ብርሃን መሪም እዝነትም ሲኾን ይገሰጹ ዘንድ ለሙሳ መጽሐፉን በእርግጥ ሰጠነው፡፡›› ቀሰስ 43

ስለሸፈዓ በሚናገረው ረዥም ሀዲስ ላይም ነብዩ ሰዐወ እንዲህ ብለዋል

( . . . « فيأتون إبراهيم فيقول : لست هُنَاكم ويذكر خطيئته التي أصابها ولكن ائتوا موسى عبدًا آتاه الله التوراة وكلمه تكليما »

“ህዝቦች ወደ ኢብራሂም ሲሄዱ እኔ ለዚህ ተገቢ አይደለሁም በማለት ስለ ኃጢአቱም ከተናገረ በኃላ ወደ ሙሳ ሂዱ ምክንያቱም እሱ አላህ ተውራትን የሰጠውና አላህም ያናገረው ሰው ነው” ይላቸዋል፡፡[1] ቡኻሪ 741ዐ ሙስሊም 193

አላህ ተውራትን በሰሌዳ ተፅፎ እንደሰጠው እንዲህ ሲል ይናገራል

{ وَكَتَبْنَا لَهُ فِي الْأَلْوَاحِ مِنْ كُلِّ شَيْءٍ مَوْعِظَةً وَتَفْصِيلًا لِكُلِّ شَيْءٍ } (الأعراف : 145)

‹‹ለእርሱም በሰሌዳዎቹ ላይ ከነገሩ ሁሉ ግሳጼንና ለነገሩም ሁሉ ማብራራትን ጻፍንለት፡፡›› አል አዕራፍ 145

አቡሑረይራ በአስተላለፉት ስለአደምና ሙሳ ክርክር በሚናገረው ሀዲስ ላይም ነብዩ ሰዐወ እንዲህ ይላሉ

( . . . « قال له آدم : يا موسى اصطفاك الله بكلامه وخط لك التوراة بيده » أخرجاه في الصحيحين

 “አደምም አለው ሙሳ ሆይ አላህ በንግግሩ መረጠህ እንዲሁም ተውራትን በእጁ ፃፈልህ…”[ቡኻሪ 6614 ሙስሊም 2652]

ተውራት ለኢስራኤል ልጆች ከተሰጡ መፅሐፎች ሁሉ ትልቁ ሲሆን ዝርዝር ህግጋቶቻቸውንም የሚያብራራ ነው፡፡ ከሙባ በኃላም የመጡ ነቢያት የሚመሩት በተውራት ነበር፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል

{ إِنَّا أَنْزَلْنَاالتَّوْرَاةَ فِيهَا هُدًى وَنُورٌ يَحْكُمُ بِهَا النَّبِيُّونَ الَّذِينَ أَسْلَمُوا لِلَّذِينَ هَادُوا وَالرَّبَّانِيُّونَ وَالْأَحْبَارُ بِمَا اسْتُحْفِظُوا مِنْ كِتَابِ اللَّهِ وَكَانُوا عَلَيْهِ شُهَدَاءَ } (المائدة : 44)

‹‹እኛ ተውራትን በውስጥዋ መምሪያና ብርሃን ያለባት ስትኾን አወረድን፡፡ እነዚያ ትዕዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ፡፡ ሊቃውንቱና ዐዋቂዎቹም ከአላህ መጽሐፍ እንዲጠብቁ በተደረጉትና በርሱም ላይ መስካሪዎች በኾኑት (ይፈርዳሉ)፡፡›› አል ማኢዳህ 44

ይሁንና በሚከተለው ጥናት እንደሚብራራው አይሁዶች ተውራትን በመበረዝ አዛብተውታል፡፡

ለ. ኢንጂል፡- ኢኝጂል በመርየም ልጅ ኢሳ ላይ የወረደ መፅሐፍ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል

{ وَقَفَّيْنَا عَلَى آثَارِهِمْ بِعِيسَى ابْنِ مَرْيَمَ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ التَّوْرَاةِ وَآتَيْنَاهُ الْإِنْجِيلَ فِيهِ هُدًى وَنُورٌ وَمُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ التَّوْرَاةِ وَهُدًى وَمَوْعِظَةً لِلْمُتَّقِينَ } (المائدة : 46)

‹‹በፈለጎቻቸውም (በነቢያቶቹ ፈለግ) ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲኾን አስከተልን፡፡ ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሳጭ ሲኾን ሰጠነው፡፡›› አል ማኢዳህ 46

አንቀፁ ላይ እንደተገለፀው ኢንጂል ለተውራት መስካሪ በመሆንና እሱንም በመስማማት የወረደ ነበር፡፡ አንዳንድ ዑለማዎች እንደሚሉት ኢንጂል ተውራትን የሚለየው በውስን ድንጋጌዎች ብቻ ነበር፡፡ ይህንንም አላህ ስለ መሲህ (ዒሳ) ሲናገር እንዲህ በማለት ገልፆታል፡፡

{ وَلِأُحِلَّ لَكُمْ بَعْضَ الَّذِي حُرِّمَ عَلَيْكُمْ } (آل عمران : 50)

‹‹በእናንተ ላይ እርም የተደረገውን ከፊል ለእናንተ እፈቅድ ዘንድ፡፡» አል ዒምራን 5ዐ

አላህ በቁርአን ላይ ተውራትና ኢንጂል ነብዩን በማበሰር እንደተናገሩ እንዲህ በማለት ይገልፃል፡፡

{ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ الرَّسُولَ النَّبِيَّ الْأُمِّيَّ الَّذِي يَجِدُونَهُ مَكْتُوبًا عِنْدَهُمْ فِي التَّوْرَاةِ وَالْإِنْجِيلِ } (الأعراف : 157)

‹‹ለእነዚያ ያንን እነሱ ዘንድ በተውራትና በኢንጂል ተጽፎ የሚያገኙትን የማይጽፍና የማያነብ ነቢይ የኾነውን መልክተኛ የሚከተሉ ለኾኑት (በእርግጥ እጽፍለታለሁ)፡፡›› አል አዕራፍ 157

ኢንጂልም ቢሆን እንደተውራት የተበረዘ መሆኑን በሚከተለው ጥናት ይጠቀሳል፡፡

መ. ዘቡር፡- ዘቡር በዳውድ ላይ የወረደ መፅሐፍ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል

{ وَآتَيْنَا دَاوُدَ زَبُورًا } (السماء : 163)

‹‹ለዳውድም ዘቡርን ሰጠነው፡፡›› ኒሳእ 163

ቀታዳህ የዚህን አንቀፅ ትርጉም ሲናገሩ “ዘቡር አላህ ለዳውድ ያስተማረው ዱዓ የአላህ ምስጋናና ውዳሴ እንጂ ሀላል ሀራም ግዴታዎችና ህግጋቶች እንዳልነበር ይነገረን ነበር” ይላል፡፡

ሠ. የኢብራሂም ፅሁፍ

በቁርአን ሁለት ቦታዎች ላይ የተጠቀሰ ሲሆን አንደኛው ሱረቱ ነጅም

{ أَمْ لَمْ يُنَبَّأْ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَى }{ وَإِبْرَاهِيمَ الَّذِي وَفَّى }{ أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَى }{ وَأَنْ لَيْسَ لِلْإِنْسَانِ إِلَّا مَا سَعَى } (النجم : 36-39)

‹‹ይልቁንም በዚያ በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ ባለው ነገር አልተነገረምን? በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም (ጽሑፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?) [(እርሱም ኃጢያት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢኣት አትሸከምም፡፡ ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም፡፡›› ነጅም 36-39

ሁለተኛው ሱረቱል አዕላ

{ قَدْ أَفْلَحَ مَنْ تَزَكَّى }{ وَذَكَرَ اسْمَ رَبِّهِ فَصَلَّى }{ بَلْ تُؤْثِرُونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا }{ وَالْآخِرَةُ خَيْرٌ وَأَبْقَى }{ إِنَّ هَذَا لَفِي الصُّحُفِ الْأُولَى }{ صُحُفِ إِبْرَاهِيمَ وَمُوسَى } (الأعلى : 14- 19)

‹‹የተጥራራ ሰው በእርግጥ ዳነ፡፡ የጌታውንም ስም ያወሳና የሰገደ፡፡ ይልቁንም ቅርቢቱን ሕይወት ትመርጣላችሁ፡፡ መጨረሻይቱ (ሕይወት) በላጭ ሁል ጊዜ ዘውታሪም ስትኾን፡፡  ይህ በፊተኞቹ መጻሕፍት ውስጥ ያልለ ነው፡፡ በኢብራሂምና በሙሳ ጽሑፎች ውስጥ፡፡›› አል አዕላ 14-19

ረ. ቁርአን፡- ቁርአን በነብዩ ሙሐመድ ሰዐወ ላይ የወረደ ሲሆገ ከበፊቱ ለነበሩት መስካሪ የሁሉም የበላየ ፈራጅና ሁሉን ሰርዞ የሚተኻ መፅሐፍ ነው፡፡ መጨረሻ ላይ የወረደና ከሁሉም በላጭ ከሁሉም ይበልጥ የተሟላ መፅሐፍ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል

{ وَأَنْزَلْنَا إِلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ الْكِتَابِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ } (المائدة : 48)

‹‹ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን፡፡›› አል ማኢዳህ 48

{ قُلْ أَيُّ شَيْءٍ أَكْبَرُ شَهَادَةً قُلِ اللَّهُ شَهِيدٌ بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ وَأُوحِيَ إِلَيَّ هَذَا الْقُرْآنُ لِأُنْذِرَكُمْ بِهِ وَمَنْ بَلَغَ } (الأنعام : 19)

«በምስክርነት ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ማነውበላቸው፡፡ (ሌላ መልስ የለምና) «አላህ ነው፡፡ በእኔና በእናንተ መካከል መስካሪ ነው፡፡ ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውን ሰው ሁሉ በርሱ ላስፈራራበት ወደኔ ተወረደ፡፡›› አል አንዓም 19

{ تَبَارَكَ الَّذِي نَزَّلَ الْفُرْقَانَ عَلَى عَبْدِهِ لِيَكُونَ لِلْعَالَمِينَ نَذِيرًا } (الفرقان : 1)

‹‹ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ያወረደው (አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው፡፡›› ፉርቃን 1

ቁርአን ብዙ ስሞች አሉት ቢሆንም ቁርአን፣ ፉርቃን፣ ኪታብ፣ ተንዚልና ዚክር የጐላ ስሞቹ ናቸው፡፡በአጠቃላይ በነዚህ ሁሉ መፃህፍት በስሞቻቸው ፣ በወረደባቸውና ስለነሱ በቁርአንና በሀዲስ የተነገሩ ነገሮች ሁሉ ማመን ግዴታ ነው፡፡

  1. ሁሉም መፃህፍት በቁርአን እንደተሰረዙና ማንኛውም ሰውም ሆነ ጋኔን የቀደምት ባለ መፅሐፎችም ሆኑ ሌሎች ቁርአን ከወረደ በኃላ ከሱ ውጭ በሆነ መፅሐፍ አላህን ማምለክ ወይም መፋረድ እንደማይፈቀድ ማመን፡፡ ይህን የሚያመላክቱ የቁርአንና የሀዲስ መረጃዎች ብዙ ናቸው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል

{ تَبَارَكَ الَّذِي نَزَّلَ الْفُرْقَانَ عَلَى عَبْدِهِ لِيَكُونَ لِلْعَالَمِينَ نَذِيرًا } (الفرقان : 1)

‹‹ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ ለዓለማት አስፈራሪ ይኾን ዘንድ ያወረደው (አምላክ) ክብርና ጥራት ተገባው፡፡›› ፉርቃን 1

{ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ قَدْ جَاءَكُمْ رَسُولُنَا يُبَيِّنُ لَكُمْ كَثِيرًا مِمَّا كُنْتُمْ تُخْفُونَ مِنَ الْكِتَابِ وَيَعْفُو عَنْ كَثِيرٍ قَدْ جَاءَكُمْ مِنَ اللَّهِ نُورٌ وَكِتَابٌ مُبِينٌ }{ يَهْدِي بِهِ  اللَّهُ مَنِ اتَّبَعَ رِضْوَانَهُ سُبُلَ السَّلَامِ وَيُخْرِجُهُمْ مِنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ بِإِذْنِهِ وَيَهْدِيهِمْ إِلَى صِرَاطٍ مُسْتَقِيمٍ } ( المائدة : 15 ، 16)

‹‹የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! ከመጽሐፉ ትሸሽጉት ከነበራችሁት ነገር ብዙውን ለእናንተ የሚገልጽ ከብዙውም የሚተው ሲኾን መልክተኛችን (ሙሐመድ) በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ ብርሃንና ገላጭ መጽሐፍ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ አላህ ውዴታውን የተከተሉትን ሰዎች የሰላምን መንገዶች በእርሱ ይመራቸዋል፡፡ በፈቃዱም ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል፡፡ ወደ ቀጥተኛም መንገድ ይመራቸዋል፡፡›› አል ማኢዳህ 15-16

አላህ ለነብዩ በመፃህፍት ባለቤቶች መካከል በቁርአን እንዲፈርዱ ሲያዝ እንዲህ ይላል

{ فَاحْكُمْ بَيْنَهُمْ بِمَا أَنْزَلَ اللَّهُ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ عَمَّا جَاءَكَ مِنَ الْحَقِّ } (المائدة : 48)

‹‹በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ፡፡ እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል፡፡›› አል ማኢዳህ 48

{ وَأَنِ احْكُمْ بَيْنَهُمْ بِمَا أَنْزَلَ اللَّهُ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ وَاحْذَرْهُمْ أَنْ يَفْتِنُوكَ عَنْ بَعْضِ مَا أَنْزَلَ اللَّهُ إِلَيْكَ } (المائدة : 49)

‹‹በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ፡፡ ፍላጎቶቻቸውንም አትከተል፡፡ አላህም ወደ አንተ ካወረደው ከከፊሉ እንዳያሳስቱህ ተጠንቀቃቸው (ማለትን አወረድን)፡፡›› አል ማኢዳህ 49

ጃቢር ኢብን አብደላ በአስተላለፉት ሀዲስ “ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ከመፅሃፍ ባለቤቶች ካገኘው የተወሰነ ፅሁፍ በመያዝ ወደ ነብዩ ሰዐወ በመሄድ ሲያነቡ ነብዩ ሰዐወ በቁጣ እንዲህ አሉት

« أمتهوكون فيها يا ابن الخطاب والذي نفسي بيده لقد جئتكم بها بيضاء نقية ، لا تسألوهم عن شيء فيخبروكم بحق فتكذبوا به ، أو بباطل فتصدقوا ، والذي نفسي بيده ، لو أن موسى كان حيا ، ما وسعه إلا أن يتبعني » رواه أحمد والبزار والبيهقي

“ትደናበራላችሁ እንደየኸጣብ ልጅ እኔኮ ጥርት ያለ መመሪያ ነው ይዤላችሁ የመጣሁት እነሱን አንዳች ነገር እንዳትጠይቁ ምናልባት ሐቅን ነግሯችሁ ልታስተባብሉ ወይም ሐሰትን ነግሯችሁ ልታምኑ ትችላላችሁና ነፍሴ በእጁ ባለው ጌታ እምላለሁ ሙሳ እንኳን ህያው ቢሆን እኔን ከመከተል ውጭ ሌላ አማራጭ መውሰድ አይችልም፡፡”[ሙስነድ አህመድ 3/387 ከሽፋል አስታር 134 ሹዐቡል ኢማን 177]

ይህ በጥቅሉ በመፅሀፎች ላይ ሊኖር የሚገባ እምነቶች ሲሆን በቁርአን በተለየ መልኩ መታመን ያሉባቸው እምነቶች ለብቻ ይጠቀሳል፡፡