ከሠለፎች ማኅደር

0
410

 ቀደምቶቻችን ሶሃቦችም ሆኑ እነሱን በመልካሙ የተከተሉት ተተኪ ትውልዶች አንደበታቸውና ተግባራቸው እኩል እንዲራመድ እጅግ ይጥራሉ። እንደ ጥንቃቄያቸውና ልፋታቸውም ተሳክቶላቸዋል።

 ዙበይድ አልያሚ የታላቁን ሰሃቢይ የአብደላህ ኢብን መስዑድን የማስጠንቀቂያ ንግግር በመጥቀስና የራሰቸውን ጥንቃቄ በማውሳት ይመክሩናል። አላህ ይዘንላቸው ስራቸውንም ይውደድላቸው።

እንዲህም ይላሉ

{ የኢብኑ መስዑድ ንግግር ለሀያ አመታት ዝም አሰኘችኝ። እሷም

☞  “ንግግሮቹ  ከተግባሩ የማይስማማ ሰው ራሱን ያስጠንቅቅ❗” የምትለዋ ናት። }【ዑዩኑል-አኽባር: 2/179】       

  እኛም የአንድ እለት ተግባርና ንግግራችንን እንኳ ብንመረምር ምን ያህሉ እንደሚለያይ እንረዳ ይሆናል። ከዚያም እድሜ ልካችንን በዝምታ ማሳለፍን እንመርጥ ይሆናልና በራሳችን ላይ እንዝመት❗

♣♣አ ን ዋ ሽ

♣♣አ ን ቅ ጠ ፍ

♣♣አ ና ስ መ ስ ል

♣♣ቃ ላ ች ን ን  እ ን ጠ ብ ቅ

♣♣ቀ ጠ ሮ ዎ ች ን  እ ና ክ ብ ር

♣♣የ ማ ን ተ ገ ብ ረ ው ን  አ ና ው ራ

♣♣እኛ የማንችለውን በሌሎች አንጫን

አላህ ልቦናችንን ያፅዳልን፣ አንደበታችንንም ይጠብቅልን፣ ከተግባሮቻችንም ያስማማልን።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here